1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ፍሮንቴክስ» የቀረበበትን ወቀሳ ማመኑ

ዓርብ፣ ጥቅምት 8 2006

በእንግሊዘኛው ምህፃር «ፍሮንቴክስ» የተባለው ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የድንበር ጥበቃ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን በመመለስ የደረሰበትን ወቀሳ አመነ ።

https://p.dw.com/p/1A1mK
ምስል Sakis Mitrolidis/AFP/Getty Images

ድርጅቱ ለአንድ የጀርመን ቴሌቬዥን በሰጠው ቃለ ምልልስ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ስደተኞች ወደ ሶስተኛ ሃገራት በኃይል እንዲመለሱ መደረጉን አምኗል ። ለስደተኞች መብት የሚከራከሩ ድርጅቶች«ፍሮንቴክስ» የፈፀመው ተግባር ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን የሚፃረር ነው ሲሉ ይከሳሉ ። ሂሩት መለሰ ።

እጎአ በ2004 የተቋቋመው «ፍሮንቴክስ» ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ድንበር ጥበቃ እገዛ የሚያደርግ ድርጅት ነው ። ይኽው ድርጅት በአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብቶች ህግጋት መሠረት የህብረቱ አባል ሃገራት የድንበር አስተዳደር መስራቱን የሚከታተልና የሚያስተባብር መስሪያ ቤት ነው ።

Symbolbild Grenze Frontex
የFRONTEX አባላትምስል Sakis Mitrolidis/AFP/Getty Images

ይሁንና የስደተኞች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ የስደተኞችን መብት ይጥሳል ፤ ስደተኞቹንም ለአደጋ ያጋልጣል ። ድርጅቱን በዚህ ከሚወቅሱት የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ አባሻ ኤጀንሲ የተባለው ለስደተኞች እርዳታ የሚሰጥ ግብረሰናይ ድርጅት ይገኝበታል ። የአባሻ ኤጀንሲ ሃላፊ አባ ሙሴ ዘርዓይ ድርጅታው ፍሪሮንቴክስን የሚወቅብስበትን ምክንያት ያብራራሉ ።

ከዚያ ይልቅ እንደ አባ ሙሴ ፍሮንቴክስ በሰብዓዊነት የስደተኞች ህይወት ለመታደግ ቅድሚያ መስጠት ነበረበት ።

ፍሮንቴክስ ከአንድ ዓመት በፊት ስደተኞች ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር እንዲመለሱ በማድረግ ሂደት ኃይል በመጠቀሙ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት እርምጃው ኢሰብዓዊ ነው ሲል ብይን አሳልፎበት ነበር ። ይሁንና ምግባሩ አለመቆሙን ARD የተባለው የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያ ባደረገው ምርመራ ደርሶበታል ። በዚሁ ጉዳይ ላይ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃለ ምልልስ የሰጡት የድርጅቱ ሃላፊ ኢካ ላይቲነን ስደተኞችን በኃይል ወደ መጡበት እንዲመለሱ ማድረግ ተቀባይነት እንደሌለው ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግረዋል ።

Spanien Frontex Boot
ምስል Desiree Martin/AFP/Getty Images

ሃላፊዋ የፍሮንቴክስ የሥራ ባልደረቦችም ስደተኞችን ጠርዞ ወደ ሶስተኛ ሃገራት በመላክ ተሳትፈውበታል የሚባለውንም በአንዳንድ ሁኔታዎች አልተደረገም ለማለት አይቻልም ሲሉ አምነዋል ። በቅርቡ በኢጣልያዋ የላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ ወደ 364 የሚደርሱ ስደተኞች ህይወት ከጠፋበት የጀልባ መስጠም አደጋ በኋላ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ ፍሮንቴክስን ለማጠናከር ተስማምተዋል ። አባ ሙሴ ፍሮንቴክስ የሚጠናከረው ስደተኞችን ወደ መጡበት ለመመለስ መሆን የለበትም ይላሉ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ