1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፍንዳታ በኮንጎ ብራዛቪል

ረቡዕ፣ የካቲት 28 2004

በኮንጎ መዲና ብራዛቪል በወታደራዊ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ፍንዳታ ከደረሰ ከሶስት ቀናት በኋላ ከዛሬ ጀምሮ የነፍስ ማዳን ተግባሩ እንደማይቀጥል ባለስልጣናት አመለከቱ። በፍንዳታዉ የወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዉ የሰልጣኞች ማደሪያ በመፈራረሱ፤

https://p.dw.com/p/14GST
ምስል dapd

 በርካቶች በስሩ ሳይቀበሩ እንዳልቀሩ ስጋት አለ። ቀይ መስቀል ወደስፍራዉ ዘልቆ ለመግባት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ ሲገለፅ አደጋዉ ወደረሰበት ስፍራ የሚወስደዉ መንገድ ጥይት የማይበሳዉ ጃኬት በደረሰቡ ወታደራዊ መኮንኖች መታጠሩም ተገልጿል። ወደሁለት መቶ ሰዎች ህይወት እንደተቀጠፈበት በተነገረዉ በዚህ ፍንዳታ የተጎዱት ከአንድ ሺ ሶስት መቶ እንደሚልቁ፤ ፍንዳታዉ ባስከተለዉ እሳት መዘዝም ወደአምስት ሺ የሚሆኑት ደግሞ ቤታቸዉን ጥለዉ ለመሸሽ መገደዳቸዉ ተዘግቧል። ኮንጎም ለደረሰዉ ጉዳት በብሄራዊ ደረጃ የሃዘን ቀን አድርጋዋለች ዕለቱን።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ