1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሩሢያ

እሑድ፣ የካቲት 25 2004

ሩሢያ ውስጥ ዘጠኝ የተለያየ የሰዓት አቆጣጠር ባለባቸው አካባቢዎች ተክፋፍሎ የሚደረገው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በዛሬው ዕለትም ሲካሄድ ውሏል። በምርጫው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የቆዩት ቭላዲሚር ፑቲን ለሶሥተኛ የሥልጣን ዘመን ወደ ርዕስነቱ መመለሳቸውን በውቅቱ የሚጠራጠር የለም።

https://p.dw.com/p/14EpP
ምስል Reuters

ሩሢያ ውስጥ ዘጠኝ የተለያየ የሰዓት አቆጣጠር ባለባቸው አካባቢዎች ተክፋፍሎ የሚደረገው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በዛሬው ዕለትም ሲካሄድ ውሏል። በምርጫው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የቆዩት ቭላዲሚር ፑቲን ለሶሥተኛ የሥልጣን ዘመን ወደ ርዕስነቱ መመለሳቸውን በውቅቱ የሚጠራጠር የለም። በሰዓቱ ልዩነት መሠረት ድምጽ አሰጣጡ በሩሢያ የሩቅ ምሥራቅ አካባቢ ሲጀመር በመጨረሻ የሚመርጡት ደግሞ በስተምዕራብ በፖላንድና በሊቱዋኒያ መካከል የምትገኘው ግዛት የካሊሊንግራድ ነዋሪዎች ይሆናሉ። በታሕሣስ ወር ተካሂዶ የነበረው የም/ቤት ምርጫ መጭበርበር ባለፉት ወራት በሩሢያ ታላላቅ ከተሞች ተቃውሞን ቀስቅሶ መቆየቱ ይታወቃል። ፑቲንን በመፎካከር ለምርጫው ከቀረቡት አራት ዕጩዎች መካከል በዋናነት የሚታወቁት ኮሙኒስቱ ጌናዲይ ዙጋኖቭና ባለጸጋው ሚካኢል ፕሮኮሮቭ ናቸው። በመጨረሻ በቀረቡ የዝንባሌ መለኪያ መጠይቅ ውጤቶች መሠረት ፑቲን 60 በመቶ፤ እንዲሁም ዙጋኖቭ 15 በመቶ ድምጽ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን