1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በፈረንሣይ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2004

በፈረንሣይ ትናንት በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የፕሬዚደንት ኒኮላይ ሳርኮዚ ዋና ተፎካካሪ የሶሻሊስቱ ፓርቲ ዕጩ ፍራንስዋ ኦሎንድ 28,6 ከመቶ የመራጭ ድምፅ በማግኘት ቀዳሚውን ቦታ ሲይዙ፡ ሳርኮዚ 27,1 ከመቶ አግኝተዋል።

https://p.dw.com/p/14jmT
French Socialist party candidate Francois Hollande arrives at his campaign headquarters on the morning after the first round of the French presidential elections in Paris, France, Monday, April 23, 2012. Hollande has taken his plodding, undynamic campaign to become France's next president to within spitting distance of victory over the "hyper-president" Nicolas Sarkozy, finishing first in Sunday's initial round of voting. (Foto:Michel Spingler/AP/dapd)
ፍራንስዋ ኦሎንድምስል dapd

ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ በዕጩነት ከቀረቡት አሥር ዕጩዎች መካከል አንዱም ለከፍተኛው የሀገሪቱ ሥልጣን የሚያበቃውን የመራጭ ድምፅ ባለማግኘቱ እአአ የፊታችን ግንቦት ስድስት ቀን በፍራንስዋ ኦሎንድ እና በኒኮላ ርኮዚ መካከል የመለያው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይካሄዳል። በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ላይ በተለይ በማሪን ለ ፔን የሚመራው የቀኝ አክራሪው ፓርቲ 17,9 ከመቶ የመራጭ ድምፅ በማግኘት የሶስተኛነቱን ቦታ መያዙና በምርጫው የተሳተፈው መራጭ ሕዝብ ቁጥር ከሰማንያ ከመቶ በልጦ መገኘቱ ብዙዎችን አስገርሞዋል። የግራ ፓርቲ መሪ ዦን ሉክ ሜሎንሾ 11,1ከመቶ ፣ የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ፍራንስዋ ባይሩ ደግሞ 9,1ከመቶ  የመራጭ ድምፅ አግኝተዋል። በፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሂደት አኳያ ባጠቃላይ ስለታየው የሀገሪቱ ሕዝብ አስተያየት የፓሪስዋ ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህ ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት ቀጣዩን ማብራሪያ በስልክ ሰጥታኛለች።

ሀይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ