1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ድጋሚ ተመረጡ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 28 2005

ዩ ኤስ አሜሪካውያን ባራክ ኦባማን ሀገሪቱን ለተጨማሪ አራት ዓመታት በፕሬዚደንትነት እንዲመሩ ድጋሚ መረጡዋቸው። ቀልብ በሳበ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ነበር ዴሞክራቱ ፕሬዚደንት ከባድ የነበረውን ፉክክር ያሸነፉት።

https://p.dw.com/p/16e3r
U.S. President Barack Obama, who won a second term in office by defeating Republican presidential nominee Mitt Romney, walks out with his family to address supporters during his election night rally in Chicago, November 7, 2012. REUTERS/Jeff Haynes (UNITED STATES - Tags: POLITICS ELECTIONS USA PRESIDENTIAL ELECTION)
ምስል REUTERS

ባራክ ኦባማ በተለይ ድምፃቸውን ለየትኛው ዕጩ እንደሚሰጡ በግልጽ ባልታወቁት እና « ስዊንግ ስቴትስ» በሚባሉት ብዙዎቹ ፌዴራውያን ግዛቶች ቀንቶዋቸዋል። የድምፅ ቆጠራው ሳያበቃ በፊት ኦባማ በምርጫው ለማሸነፍ የሚያስፈልገውን የፌዴራል ግዛቶች ተወካዮችን ድምፅ ማግኘታቸው የተረጋገጠው የኦሀዮ ፌዴራዊ ግዛት ተወካዮችን ድምጽ ባገኙበት ጊዜ ነበር። የፍሎሪዳ ውጤት እስከመጨረሻው አልታወቀም ነበር፤ ምንም እንኳን በውጤቱ ላይ ምንም ለውጥ ባያመጣም። ድጋሚ የተመረጡት ፕሬዚደንት ኦባማ ውጤቱ በይፋ ከተገለጸ በኋላ ባሰሙት ንግግር፡ በምርጫው የተሳተፉትን የዩኤስ አሜሪካ ዜጎች በጠቅላላ ከልብ አመሥግነዋል።በምርጫው የተሸነፉትን ተፎካካሪያቸውን ሬፓብሊካዊውን ሚት ሮምኒን ለዩኤስ አሜሪካ ጥቅም ሲሉ አብረዋቸው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሽንፈታቸውን የተቀበሉት ሚት ሮምኒ ለኦባማ ስልክ በመደወል የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። እስካሁን ይፋ በወጣው ውጤት መሠረት፣ ፕሬዚደንት ኦባማ 303፣ ሚት ሮምኒ ደግሞ 206 የፌዴራል ግዛቶች ተወካዮች ድምፅ አግኝተዋል። ከፕሬዚደንታዊው ምርጫ ጎን ለጎን በተካሄደው የሕዝብ መምሪያ ምክር ቤት የሬፓብሊካውያኑ ፓርቲ ፡ ለአንድ ሦስተኛው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ ደግሞ የዴሞክራቶቹ ፓርቲ በድጋሚ አብላጫውን ድምፅ አግኝተዋል። የፕሬዚደንት ኦባማ ተቀናቃኝ ሬፓብሊካዊው ጆን በነር እንደገና የሕግ መምሪያው ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሆነው ተመርጠዋል።

[15456408] US-Fahne auf Halbmast zum Tod von Edward Kennedy The US national flag flies at half-mast at the US Capitol Building to observe the death of Democratic Senator Edward Kennedy of Massachusetts, in Washington DC, USA, 26 August 2009. Senator Kennedy died at his home in Hyannis Port, Massachusetts early 26 August 2009 as a result of brain cancer. Senator Kennedy was the younger brother of late US President John F. Kennedy and late New York Senator Robert Kennedy, both of whom were assassinated. Known as the ?Lion of the Senate?, Edward Kennedy was instrumental in the passage of the Civil Rights Act of 1964, the Voting Rights Act of 1965, the 1990 Americans with Disabilities Act and the 1993 Family and Medical Leave Act. EPA/MICHAEL REYNOLDS +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/dpa
--- 2012_11_07_USA_wahl_2012_700_1.psd 2012_11_07_USA_wahl_2012_460_1.psd

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ