1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖለቲከኞቹ ተለቀቁ፤ «እንታገላለን» አሉም

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2008

ፖለቲከኞቹ ዛሬ እንዳስታወቁት ከመታሠራቸዉ በፊት የጀመሩት ትግል እስር ቤት ሆነዉም አልቆመም ነበር።ወደፊትም አይቋረጥም።

https://p.dw.com/p/1IlEx

[No title]

ትናንት ከእስር ቤት የተለቀቁት ሁለት የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ትግላቸዉን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲና የሠማያዊ ፓርቲ ፖለቲከኞች ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋ በአሸባሪነት ተከሰዉ ፍርድ ቤት በነፃ ቢለቃቸዉም፤ ችሎት በመዳፈር ወንጀል ከአንድ ዓመት በላይ እስራት ተፈርዶባቸዉ ፍርዳቸዉን ትናንት ነዉ የጨረሱት።ፖለቲከኞቹ ዛሬ እንዳስታወቁት ከመታሠራቸዉ በፊት የተቀየጡት ትግል እስር ቤት ሆነዉም አልቆመም ነበር።ወደፊትም አይቋረጥም። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ዮሐነስ ገብረ እግዚአብሄር

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ