1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

10 የምዕራብ ሃገራት አምባሳደሮችን አባርራለሁ ያሉት የቱርኩ ፕሬዚዳንት  

ሰኞ፣ ጥቅምት 15 2014

የቱርክ ፕሬዝደንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ እስር ላይ የሚገኙት ኦስማን ካቫላ የተባሉ በጎ አድራጊ እንዲለቀቁ ጥሪ ያቀረቡ የአስር አገራት አምባሳደሮችን ዲፕሎማሲያዊ ከለላ እንዲያነሳ ማዘዛቸው ትልቅ ቁጣን ቀስቅሶአል።

https://p.dw.com/p/42A62
Türkei Recep Tayyip Erdogan in Eskisehir
ምስል Murat Cetinmuhurdar/Turkish Presidency/AA/picture alliance

የ62 ዓመቱ ካቫላ ከተጠረጠሩበት ክስ በቱርክ ፍርድ ቤት ነጻ ተብለዉ ነበር

የቱርክ ፕሬዝደንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ እስር ላይ የሚገኙት ኦስማን ካቫላ የተባሉ በጎ አድራጊ እንዲለቀቁ ጥሪ ያቀረቡ የአስር አገራት አምባሳደሮችን ዲፕሎማሲያዊ ከለላ እንዲያነሳ ማዘዛቸው ትልቅ ቁጣን ቀስቅሶአል። ባለፈዉ ሳምንት መገባደጃ ፕሬዝደንት ኤርዶኻን፤ ትዕዛዝ ካስተላለፉባቸዉ አስር ሃገራት መካከል የአሜሪካ፣ የጀርመን እና የፈረንሳይ አምባሳደሮች ይገኙበታል። አምባሳደሮቹ ያስተላለፉት ጥሪ በቱርክ መንግሥት "ኃላፊነት የጎደለው" ነዉ ተብሎአል።   

ኦስማን ካቫላ ተቃዋሚዎችን በገንዘብ በመደገፍ እና ባልተሳካ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ በመሳተፍ ተጠርጥረው ከታሰሩ አራት ዓመታት ገደማ ሆኗቸዋል። የ62 ዓመቱ ካቫላ ባለፈው ዓመት ከተጠረጠሩበት ክስ በቱርክ ፍርድ ቤት ነጻ ተብለው ቢለቀቁም የቱርክ መንግሥትን ለመገልበጥ በማሴር በሚል ወዲያውኑ በጸጥታ አስከባሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የአውሮጳ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ከሁለት ዓመታት በፊት ከእስር እንዲፈቱ ወስኖም ነበር።

 

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ