1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

125ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በኦሮሚያ

ማክሰኞ፣ የካቲት 23 2013

የኦሮሚያ ርዕሠ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበዓሉ ላይ ለታመደዉ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠር ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ አስቸገሪ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዉ፣ ይሁንና አሁንም ጀግና ትዉልድ ስላላት አትፈርስም ብለዋል

https://p.dw.com/p/3q79t
Äthiopien | Adwa Victory Celebration
ምስል Seyoum Getu/DW

«ታሪክ በሽለላና በፌስ ቡክ ጨዋታ አይሰራም» ሽመልስ አብዲሳ


የኢትዮጵያ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት በየአደባባዩ  የፍቅር፣የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና የአንድነትን አስፈላጊነት የተናገሩበትን 125ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ እንኳ በአንድነት አላከበሩትም።ከቀዳሚዉ ዘገባችን እንደተከታተላችሁት ብሔራዊዉ በዓል አዲስ አበባ አፄ ምኒሊክ መታሰቢያ አደባባይ ሲከበር፣ የኦሮሚያ መስተዳድር ደግሞ በዓሉን እዚያዉ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አክብሯል።የኦሮሚያ ርዕሠ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበዓሉ ላይ ለታመደዉ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠር ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ አስቸገሪ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዉ፣ ይሁንና አሁንም ጀግና ትዉልድ ስላላት አትፈርስም ብለዋል።ታሪክም በሽለላና በፌስ ቡክ ጨዋታ አይሰራም-እንደ ርዕሠ መስተዳድሩ።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ