1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

125ኛ የአድዋ ድል መታሰቢያ ዉይይት

ማክሰኞ፣ የካቲት 23 2013

ሚንስቴሩ «ሥልጡን ዉይይት ለአዲስ የተስፋ ምዕራፍ» ባለዉ ርዕስ ላይ በተደረገዉ ዉይይት ከተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች የተጋበዙ እንግዶች ተካፍለዉበታል

https://p.dw.com/p/3q6ob
Äthiopien | Adwa Victory Celebration
ምስል Yohannes Gebre Egiziabhere/DW

125ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ ዉይይት

 
የአድዋ ድል 125ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ የሠላም ሚንስቴር ያዘጋጀዉ ዉይይትም ዛሬ ተጠናቅቋል።ሚንስቴሩ «ሥልጡን ዉይይት ለአዲስ የተስፋ ምዕራፍ» ባለዉ ርዕስ ላይ በተደረገዉ ዉይይት ከተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች የተጋበዙ እንግዶች ተካፍለዉበታል።የሠላም ሚንስትር ሙፈሪያት ከማል ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የአድዋ ድል ኢትዮጵያ ለነፃነትና ለፍትሕ ፈላጊዉ ዓለም ካበረከተቻቸችዉ ስጦታዎች አንዱ ነዉ።ባለፈዉ የካቲት 20 የተጀመረዉን ዉይይት በንግግር የዘጉት ፕሬዝደንት ሳሕለወርቅ ዘዉዴ በበኩላቸዉ የዘመኑ ትዉልድ ተበደልኩ ለሚለዉ እዉቅና እንዲሰጥ፣ስሕተቱን እንዲቀበልና ላለመድገም እንዲወስን ጠይቀዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ