1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

14 የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረዛቸው

ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2008

ፓርቲዎቹን ለረዥም ጊዜ መታገሱን ያሳወቀው ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎቹ የተባሉትን ባለማድረጋቸው እንዳገዳቸው አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/1Iq5H
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 14 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ከምዝገባ መሰረዙን አስታወቀ ። የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ፓርቲዎቹ ከተሰረዙባቸው ምክንያቶች ውስጥ ራሳቸው አፅድቀው እንመራበታለን ባሉበት ደንባቸው ላይ ባስቀመጡት የጊዜ ገደብ ጠቅላላ ጉባኤ አለመጥራታቸው ፣ በኦዲተር የተረጋገጠ የሃብት ሰንድ አለማቅረባቸው እና የፅህፈት ቤቶቻቸውንና አድራሻዎች ለቦርዱ አለማሳወቃቸው ይገኙበታል ። እነዚህኑ ፓርቲዎቹ ለረዥም ጊዜ መታገሱን ያሳወቀው ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎቹ የተባሉትን ባለማድረጋቸው ማገዱን አስታውቋል ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ