1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመውሊድ በዓል በአዲስ አበባ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 11 2011

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ባስተላለፈው መልዕክት ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን  ለሃገር ሰላምና አንድነት ጸሎት በማድረግ እንዲያከብር አሳስቧል።

https://p.dw.com/p/38bXD
Äthiopien Muslime Mawlid Festival Haj Nur Hussen Mohamed Yassin
ምስል DW/G. Tedla

የመውሊድ አከባበር በአንዋር መስጊድ

1493ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል (መውሊድ)ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ እየተከበረ ነው። ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዓሉን በጸሎት እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ባህላዊ ስነ ስርዓቶች ከቤተሰብ ጋር በመሰባሰብ ሲያከብረው ውሏል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ባስተላለፈው መልዕክት ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን  ለሃገር ሰላምና አንድነት ጸሎት በማድረግ እንዲያከብር አሳስቧል። በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ በተካሄደው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ