1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

29ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት

ረቡዕ፣ ሰኔ 21 2009

29ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሚነጋገርበት ርዕስ ላይ ዝግጅት ለማድረግ በያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ የአባል ሀገራት አምባሳደሮች የሁለት ቀናት ስብሰባቸዉን አዲስ አበባ በሚገኘዉ የኅብረቱ ዋና ጽ/ቤት ጀምረዋል።

https://p.dw.com/p/2fUPI
Äthiopien Hauptqartzier der Afrikanischen Union in Addis Ababa
ምስል Reuters/T. Negeri

 

እንደተለምዶ ሁሉ ለጉባዔዉ ዝግጅት በቅድምያ በአምባሳደሮች ዉይይት የሚጀምረዉ ሥነ-ስርዓት የፊታችን  ሃሙስ እና አርብ የሚንስትሮቹ ስብሰባን በማስከተል በመጭዉ ሳምንት ሰኞና ማክሰኞ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተካሂዶ ይጠናቀቃል። በዚህ ጉባዔ የደቡብ ሱዳን ቀዉስ ዋነና የመነጋገርያ አጀንዳ ነዉ ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ አበባ የሚገኘዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከፖለቲካ ተንታኝ ከዶክተር መሐሪ ታደለ ማሩ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ ዘገባ ልኮልናል። ዶ/ር መሐሪ ታደለ ጉባዔዉ በተለይ ሰላምና መረጋጋትን በተመለከተ መቋጫ ያጣዉ የደቡብ ሱዳን ዉዝግብ እና ቀዉስ ላይ እንደሚወያይ በመግለፅ ቃለ ምልልሱን ይጀምራሉ።

 
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ