3ተኛው ዙር የግሪክ ብድር
ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2007ማስታወቂያ
የግሪክ ፓርላማ አባላት ለግሪክ የታቀደውን ሶስተኛ ዙር የብድርና እርዳታ መርሃ ግብር ተቀብለው ዛሬ አጽድቀዋል ። የግሪክ የህዝብ እንደራሴዎች መርሃ ግብሩን በ222 የድጋፍ ድምፅ የተቀበሉት ትንናት ለሊት ከተካሄደ የጋለ ክርክር በኋላ ነው ። የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ደግሞ ዛሬ በመርሃ ግብር ላይ ተወያይተው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ። መርሃግብሩ ከፀደቀ ግሪክ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ውስጥ 85 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ታገኛለች ። በምትኩ ግሪክ የወጪ ቅነሳና የቀረጥ ጭማሪ ማድረግ ይጠበቅባታል ። እነዚህን የቁጠባ እርምጃዎች በመቃወም ከ40 በላይ የግሪክ ገዥ ፓርቲ ሲሪዛ አባላት መርሃግብሩን ሳይደግፉ ቀርተዋል ። ስለ አወዛጋቢው 3ተኛው ዙር የግሪክ ብድር ና በሲሪዛ ፓርቲ አባላት መካከል ስለ ተፈጠረው ልዩነት የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ