1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የጤና ድርጅት የቪዲዬ ጉባኤ

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2012

በጉባኤው የዓለም የጤና ድርጅትና አባል ሀገራቱ ወረርሽኙን ለመከላከል ያደረጉትን ጥረትና ድክመት የሚገመግም ገለልተኛ አካል እንዲቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሷል።የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን ግን መቅደም ያለበት ወረርሽኑን መከላከል ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3cYPe
Schweiz Genf WHO Treffen | Tedros Adhanom Ghebreyesus
ምስል picture-alliance/Xinhua/WHO

73 ኛው ዓለም አቀፍ የጤና ጉባኤ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ያለፈው ሰኞ በቪዲዮ ተካሄዷል።የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት የጤና አመራሮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተሳተፉበት ይህ ጉባኤ የኮረና ወረርሽኝ ዋና መነጋገሪያ አጀንዳው ነበር። በጉባኤው የዓለም የጤና ድርጅትና አባል ሀገራቱ ወረርሽኙን ለመከላከል ያደረጉትን ጥረትና ድክመት የሚገመግም ገለልተኛ አካል እንዲቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሷል።የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን ግን መቅደም ያለበት ወረርሽኑን መከላከል ነው ብለዋል።

ገበያው ንጉሴ
ፀሐይ ጫኔ
እሸቴ በቀለ