1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

746 ታራሚ እና ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ መወሰኑ

ሐሙስ፣ የካቲት 1 2010

ከመካከላቸው በፌደራል ደረጃ በሽብር፣ በሀይማኖት አክራሪነት እና በሌሎችም የተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 417 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ መወሰኑን አቃቤ ህግን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

https://p.dw.com/p/2sNBE
Äthiopien Eskindr Nega und Andualem Arage
ምስል Serkalem Fassil

እስክንድር ነጋን እና አንዷዓለም አራጌን ጨምሮ 746 ታራሚ እና ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ መወሰኑ

የኢትዮጵያ መንግሥት 746 ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎችን ለመልቀቅ መወሰኑን ዛሬ አስታውቋል። ከመካከላቸው በፌደራል ደረጃ በሽብር፣ በሀይማኖት አክራሪነት እና በሌሎችም የተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 417 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ መወሰኑን አቃቤ ህግን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ከነዚህም ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ እንደሚገኙበት ተገልጿል። ከዚህ ሌላ የ329 ተጠርጣሪዎች ክስ እንዲቋርጥም ተወስኗል ተብሏል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ልኮልናል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ