1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

CIA እና የጋዳፊ ትብብር

እሑድ፣ ነሐሴ 29 2003

የዩናይትድ ስቴትሱ የስለላ ድርጅት CIA እና MI-6 በመባል የሚታወቀዉ የብሪታንያዉ የስለላ ድርጅት ከኮነሪል ሞአመር ጋዳፊ አገዛዝ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ኒዉዮርክ ታይምስ የተሰኝዉ የዪናይትድ ስቴትስ ጋዜጣ አጋለጠ።

https://p.dw.com/p/RjtL
ምስል AP


ሰሞኑን ሊቢያ ትሪፖሊ ዉስጥ የተገኘዉ ሰነድ ሁለቱ የስለላ ድርጅቶች በአሸባሪነት የተጠረጥሩ ግለሰቦችን በሊቢያ እስር ቤቶች ዉስጥ ይመረምሩ እንደ ነበር ያረጋግጣል። ሰነዱ የተገኘዉ በቀድሞዉ የሊቢያ የዉጭ ጉዳይ እና የስለላ ድርጅት ሃላፊ ሙሳ ኩሳ ቤሮ ዉስጥ እንደ ነበር ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በማያያዝ ዘግቦአል።
በሌላ በኩል የጀርመን የፀጥታ ባለስልጣናት ከጋዳፊ የስለላ ድርጅት መረጃዎችን ያገኙ እንደነበር ቢልድ የተሰኝዉ የጀርመን ጋዜጣ ዛሪ እሁድ ባወጣዉ እትሙ አስፍሮአል። የጀርመን የቀድሞዉ የስለላ ተግባር አቀናባሪ Bernd Schmidbauer ቢልድ ለተሰኘዉ የጀርመን ጋዜጣ እንደገለጹት ከጋዳፊ መንግስት ይገኙ የነበሩት መረጃዎች በመጀመርያ ደረጃ ፀረ-ሽብር ትግል እና የጀርመንን የፀጥታ ጥቅም ይመለከቱ ነበር።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን