1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

DW የለውጥ ሂደቱ ተጓዳኝ

ሐሙስ፣ መጋቢት 19 2011

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የጀመሩት የማሻሻያ አንድ ዓመት ከሆነው በኋላ DW ኢትዮጵያ ውስጥ እንቅስቃሴውን ይበልጥ በማስፋፋት ላይ ነው። የDW ዳይሬክተር መቶ ሚሊየን ሕዝብ ባለባት የምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ስልታዊ ጠቃሚ ሀገር ኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ባካሄዱትበት ወቅት የተለያዩ የራዲዮ እና የኢንተርኔት ተጓዳኝነት ውሎችን ተፈራርመዋል።

https://p.dw.com/p/3Fim3
DW-Intendant Peter Limbourg  und DW-Delegation in Äthiopien
ምስል DW/L. Schadomsky

ከተጓዳኞች መካከል ዝናን ያተረፈው ሸገር ኤፍ ኤም፣ አሃዱ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም እና አፍሮ ኤፍ ኤም ይጠቀሳሉ። የሸገር ኤፍ ኤም ሥራ አስኪያጅ መዓዛ ብሩ «ዶይቼ ቬለ በሚያቀርባቸው ሚዛናዊ እና ጠንካራ ዘገባዎች የተከበረ ነው።» ብላለች። የታዋቂው የኢትዮ ኤፍ ኤም ሥራ አስኪያጅ ሰይፉ ፋንታሁን በበኩሉ «በተለይ የመረጃዎች አጠራጣሪነት ሲከሰት DW ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ነው።» ሲል ገልጿል። ለበርካታ አስርት ዓመታት በአጭር ሞገድ ብቻ ይሰራጭ የነበረው የአማርኛው ፕሮግራም በቀደመው የመንግሥት አስተዳደር ስልታዊ በሆነ መንገድ በመታፈን ሲደናቀፍ ነበር። በኢትዮ ኤፍ ኤም እና በአሃዱ ራዲዮ የDW ተወዳጅ ዝግጅቶች ዳግም መሰራጨት ጀምረዋል። በዚያም ላይ በተደረገው የትብብር ስምምነት መሠረት የፌስቡክ እና የመጀመሪያው የቴሌቪዥን የቅብብል ስርጭት ይፋ ተደርጓል። ፒተር ሊምቡርግ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የዲ ደብልዩ ዘጋቢዎች ጋር ስብሰባ ባካሄዱበት ወቅትም «ለዶይቼ ቬለ እዚህ የሚሰጠው ከፍተኛ ስፍራ እኛን አኩርቶናል።» ብለዋል። «በጠንካራ እና ሚዛናዊ አዘጋገብም የዚህ አስቸጋሪ የለውጥ ሂደት ተጓዳኝ መሆን እንፈልጋለን» ሲሉም አክለዋል።
DW በዚህ ሂደት የሀገር ውስጥ ዘጋቢዎቹን ቁጥር ከሁለት ወደ ስምንት ከፍ አድርጓል። ከዓመታት ጥረት በኋላ አዲሱ መንግሥት ለአማርኛው አገልግሎት ለስድስት ዘጋቢዎች ፈቃድ ሰጥቷል። ይህም DW አሁን በጎሳ ግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን አስመልክቶ ተከታታይ ዘገባዎች ለማቅረብ አስችሎታል። አዲሶቹ ዘጋቢዎች ስማርት ስልኮችን ተጠቅመው የቪዲዮ ዘገባዎችን የሚያጠናቅሩበት የአጭር ጊዜ ስልጠና እንዲያገኙ በመደረጉም በምስል የተደገፉ ዘገባዎችን እያቀረቡ ነው። በምሳሌነትም በቅርቡ የተከሰከሰውን የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ገጠመኝ መጥቀስ ይቻላል። አንዳንዴም ዘጋቢዎቻችን ለአደጋ የተጋጡበት አጋጣሚም ይታያል። ከመካከላቸው አንዱ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በወጣት ታጣቂ ኃይል ጥቃት ደርሶበት የሥራ መሣሪያውንም ተቀምቷል። በስብሰባው ወቅት ሥራ አስኪያጅጁ ሊምቡርግ የተፈፀመው ጥቃት ዘጋቢውን ለከባድ ጉዳት ሳይዳርግ በማለፉ እፎይታቸውን  ገልጸዋል። 
አዳዲሶቹ ተጓዳኝ የመገናኛ ብዙሃንም ሆኑ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከDW አካዳሚ የስልጠና ድጋፍ ጠይቀዋል። በጋዜጠኝነት ሆነ በመንግሥት የኮሙኒኬሽን ሙያ ዘርፍ የደረጃ ጥራት ክፍተት አለ። የDW አካዳሚ በያዝነው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለኢትዮጵያ አዲስ መርሃግብር ይፋ ያደርጋል። 

DW-Intendant Peter Limbourg  und DW-Delegation in Äthiopien
ምስል DW/L. Schadomsky
DW-Intendant Peter Limbourg  und DW-Delegation in Äthiopien
ምስል DW/L. Schadomsky


ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊምቡርግ እና የDW ልዑካን በተጓዳኝ በመገናኛ ብዙሃኑ ሚና ካላቸው፣ እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ እና በንግድ ዘርፍ ከተሰማሩ ሴቶች ጋር ተወያይተዋል። በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ቫግነር ባዘጋጁት የክብ ጠረጴዛ ውይይት ኢትዮጵያን የወከሉት ወገኖች ስለሽግግር ሂደቱ መሰናክሎች፣ ስለመረጃዎች መዛባት እና ተጠያቂነት ስለመጥፋቱ አንስተዋል። የሕግ ባለሙያ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና የአማራጭ ኖቤል ተሸላሚዋ የትነበርሽ ንጉሤ፣ የ42 ዓመቱ የለውጥ አራማጁ ዐቢይ ኢትዮጵያን ለአስርት ዓመታት ከተቀፈደደችበት አገዛዝ «ወደ ፍቅር አገዛዝ » አምጥተዋታል ብላለች። አሁን በሀገሪቱ የሕግ የበላይነት የሚያስፈልግበት ወሳኝ ወቅት መሆኑንም አሳስባለች። 
ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘው የDW የልዑካን ቡድን የአስተዳደር ዳይሬክተሯ ባርባራ ማሲንግ፣ የአፍሪቃ ዘርፍ ተጠሪ ዜፋና ኢብራሂም ዛወር፣ የDW አካዳሚ ምክትል ኃላፊ፣ የአፍሪቃ ፕሮግራም ኃላፊ ክላውስ ሽቴከር እንዲሁም የአማርኛ አገልግሎት ኃላፊ ሉድገር ሻዶምስኪ ያካተተ ነው።

Partnerschaftsabkommen mit Sheger FM Abebe Balcha und Peter Limbourg
ምስል DW/L. Schadomsky

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ