1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«FB» በጀርመን ያለዉ እንቅስቃሴ እንዲጠብ ተደረገ

ሐሙስ፣ ጥር 30 2011

ዩናይትድ ስቴትስ የሆነዉ የ«FB» አገልግሎት በጀርመን ሃገር ያሉ ተጠቃሚዎቹን መረጃ ከሚገባዉ በላይ በመሰብሰብ እና በየፈርጁ በማስቀመጥ ያላግባብ ተጠቅሟል ሲሉ በጀርመን መሥራያ ቤቶች እና ድርጅቶችን የሚቆጣጠረዉ ባለሥልጣን መስራያ ቤት አስታወቀ። በጀርመን የፊስቡክ አገልግሎት በተለይ መረጃን ያላግባብ በመሰብሰቡ እንቅስቃሴዉ ገደብ ተደርጎበታል።

https://p.dw.com/p/3CwJX
Jahresrückblick 2010 - Verbraucherzentrale verklagt Facebook
ምስል picture alliance / dpa

በፊደራል ጀርመን መሥርያ ቤቶች  እና  ድርጅቶች የተሰጣቸዉን ሥልጣን እና ኃላፊነት በአግባቡ መጠቀማቸዉን የሚመረምረዉ ባለሥልጣን መስርያ ቤት በጀርመንኛ አጠራሩ  «Bundeskartellamt» «FB» ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን መረጃ ካላግባብ ሰብስቧል ሲል በጀርመን ፌስቡክ ያለዉን እንቅስቃሴን ማጥበቡ ገለፀ። የዩናይትድ ስቴትስ የሆነዉ የ«FB» አገልግሎት በጀርመን ሃገር ያሉ ተጠቃሚዎቹን መረጃ ከሚገባዉ በላይ በመሰብሰብ እና በየፈርጁ በማስቀመጥ ያላግባብ ተጠቅሟል ሲሉ በጀርመን መሥራያ ቤቶች እና ድርጅቶችን የሚቆጣጠረዉ ባለሥልጣን መስራያ ቤት ዋና ተጠሪ አንድርያስ ሙንድ ዛሬ ተናግረዋል። ዋና መስራያ ቤቱን ቦን ከተማ ያደረገዉ ይህ የጀርመን ባለስልጣን መስራያ ቤት በጀርመን የፊስቡክ አገልግሎት በተለይ መረጃን በመሰብሰብ ረገድ ገደብ ተደርጎበታል ብሏል። በጀርመን እንደ «ሜሴንጀር«  «ዋትስ አፕ» «የፎቶግራፍ ማከፓቻን» የመሳሰሉ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ሁሉ ፊስቡክ በመጠቅለሉ እና ከሁሉም አገልግሎቶች የሚገኘዉ መረጃ በአንድ ቋት በመከማቸቱ ፌስቡክ ገበያዉን በሞኖፖል መቆጣጠሩን ይፋ በማድረግ የጀርመኑ ባለሥልጣን ቢሮ  ተቃዉሞታል። የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካዉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቡድን ፌስቡክ የጀርመን ባለስልጣን መስርያቤት ርምጃን በመቃወም ክስ መመስረት እንደሚፈልግ ተዘግቦአል።    

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ