1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Karibuni - የአለም ሙዚቃ ለህጻናት ሰላም

እሑድ፣ ኅዳር 22 2000

ሆያ ሆዪ፣ ሆ! ተዉ ስጠኝና ልሂድልህ እንደ አሮጌ ጅብ አልቹህብህ! ቡሄ፣ ለመስከረም መባቻ በተለይ ልጆች ሳለን የምናዜመዉ አገረሰባዊ ዜማችን በጀርመነኛ አንድ በአንድ ተተርጉሞ፣ ዜማዉ ትርጉሙን ሳይስት፣ በጀርመን በሙዚቃ አልብም ተቀርጾ ከዝያም አልፎ ፈረንጁን ሆያ ሆዮ ሲያስረግጥ ማየቱ ለኛ ለኢትዮጽያዉያን ኩራት ይመስለናል።

https://p.dw.com/p/E0ly
ምስል DW / Azeb Tadesse Hahn
በኢትዮጽያ ጥንታዊ ናቸዉ ከሚባሉት አገረሰባዊ ዜማዎች ሆያ ሆዪ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአለም ቋንቋዎች የተረጎመዉ፣ ኢትዮጽያዊ ተረቶች፣ ባህላዊ ወጎች ተተርጉመዉ ከአማረኛ ቋንቋ ጋር በማወቀናበር በሙዚቃ አልብም ወጥቶአል። አዘጋጅና አቅራቢ ኢትዮጽያዊትዋ ጆሴፊነ ክሮንፍሊ ስትሆን በተለይ በልጅነቴ እናቴ የሰጠችኝ የናትነት ፍቅር የኢትዮጽያን ባህል ለአለም እንዳስተዋዉቅ ገፋፍቶኛል ትላለች። አዜብ ታደሰ፣ ጆሲፊነ ክሮንፍሊን በባህል መድረክ ይዛት ቀርባለች መልካም ቆይታ