1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

M23 ከያዛቸው አካባቢዎች መልቀቅ መጀመሩ

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2005

የM23 አማጺያን ከጎማ እንዲወጡ ከመወሰኑ በስተቀር የተኩስ አቁም ስምምነት እስካሁን አልተደረሰም። በሌላ በኩል የM23 አማጺያን የፖሊቲካ ዦን ማሪ ሩጋ ፣ የኮንጎ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ አማጺያኑ የጠየቁትን ሲያሟሉ ብቻ ከጎማ እንደሚወጡ ተናግረዋል፣

https://p.dw.com/p/16rok
Congolese Revolutionary Army (CRA) rebel fighters stand guard as leader of the March 23 Movement (M23) Jean-Marie Runiga arrives in his car to address media in Goma November 27, 2012. Rebels in Democratic Republic of Congo said on Tuesday they would withdraw from the eastern city of Goma if President Joseph Kabila agreed to their demands, which the Congolese government was quick to dismiss as a farce. REUTERS/James Akena (DEMOCRATIC REPUBLIC OF CONGO - Tags: CIVIL UNREST POLITICS MILITARY)
ምስል Reuters

ባለፈው ሳምንት ምስራቅ ኮንጎ የምትገኘውን የጎማ ከተማንና ባከባቢዋ የሚገኙ መንደሮችን የተቆጣጠሩት አማጺያን ከያዙት አከባቢ ለቀው እየወጡ መሆናቸውን ምልክቶች መታየት ጀምረዋል። የአማጺያኑ ከጎማ የመውጣት ዜና የተሰማው ከትናንት ወዲያ በአማጺያኑ የጦር መሪና በምስራቅ አፍሪቃ ቡድን የጦር አዛዦች መካከል ዩጋንዳ መዲና ካምፓላ ከተደረሰው ስምምነት ነበር። አማጺያኑ ነገ ጎማን ሙሉ በሙሉ ይለቃሉ ተብሉ ይጠበቃል። ዝርዝሩን ገመቹ በቀለ ያቀርብልናል።

የM23 አማጺያን አመጽ፣ በብዚ ሺ የሚቆጠሩ የምስራቅ ኮንጎ ዜጎች ከቀዬያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል። በቅርቡ አማጺያኑ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎን ለመቆጣጠር ያደረጉት ፈጣን የጦር ዘመቻ ምናልባት አሁንም ሌላ ግጭት ይቀሰቅሳል የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር።

የM23 የጦር መሪን ሱልጣኒ ማኬንጋን ጠቅሶ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ባሳለፍነው ሰኞ በካምፓላ ዩጋንዳ በተደረሰው ስምምነት መሰረት፣ ዛሬ ጧት አማጺያኑ ቢበዛ በሶስት ቀናት ውስጥ ከጎማ በ20 ኪሎመትር ርቀው መውጣት ይኖርባቸዋል። የዩጋንዳ ጦር አዛዥ አሮንዳ ንካይሪማ፣ አማጺያኑ የፊታችን ሐሙስ ረፋድ ላይ ጎማን ሙሉ ለሙሉ ለቀው እንደሚወጡ በትናንትናው እለት ተናግረዋል፣

Leader of the March 23 Movement (M23) Jean-Marie Runiga waves to supporters as he arrives to address media in Goma November 27, 2012. Rebels in Democratic Republic of Congo said on Tuesday they would withdraw from the eastern city of Goma if President Joseph Kabila agreed to their demands, which the Congolese government was quick to dismiss as a farce. REUTERS/James Akena (DEMOCRATIC REPUBLIC OF CONGO - Tags: CIVIL UNREST POLITICS)
ዦን ማሪ ሩኒጋምስል Reuters
M23 rebels patrol around Congo's Central Bank in Goma, eastern Congo, Monday Nov. 26, 2012. Regional leaders meeting in Uganda called for an end to the advance by M23 rebels toward Congo's capital, and also urged the Congolese government to sit down with rebel leaders as residents fled some towns for fear of more fighting between the rebels and army. (AP Photo/Jerome Delay)
ምስል dapd
Congolese M23 rebel soldiers are seen on the road to Rushuru near Buhumba some 25 kilometers (16 miles) north of Goma, Thursday, Nov. 22, 2012. Rebel spokesman Lt. Col. Vianney Kazarama vowed Thursday that the fighters would press forward toward seizing the strategic eastern town of Bukavu, which would mark the biggest gain in rebel territory in nearly a decade if it were to fall. (AP Photo/Jerome Delay)
የ M23 አማጽያንምስል dapd



«የመከላከያ ኃይሉ ኃላፊ፣ ከኮንጎ ጦር ኃልይና ከM23 አማጺያን አመራሮች ጋር ትናንት ተገናኝተው፣ M23 ጎማን ለቆ የመውጣት እቅድ እንደሚጀምር አሳውቀዋቸዋል። ይህን ነበር ትናንት የተወያየነው። ዛሬ እኩለ ቀን ላይ፣ የM23 አማጺያን ከጎማ ወጥተው አንዳንድ ወታደራዊ ጠቀሜታ ወዳላቸው ይዞታዎች መሄድ ይጀምራሉ። የአየር መንገዱን የተቆጣጠሩ በመቶዎች የሚቆጣጠሩ ወታደሮች እዚያው ይቆያሉ። ከተማዋን የመልቀቁም ሂደት በ48 ሰዓታት ውስጥ ይጠናቀቃል።»

ጎማን የመልቀቁ ስምምነት በዩጋንዳ ዋና ከተማ ከተደረሰ ወዲህ፣ የምስራቅ አፍሪቃ የጦር አዛዦች፣ አማጺያኑ በማዕድን ሐብቱ የታወቀውን የኪቩ ግዛት ዋና ከተማ እንዲለቁ ለመልቀቅ ስለተደረሰው ስምምነት አፈጻጸም ለመመርመር የፊታችን ዓርብ ጎማ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።


አማጺያኑ ከጎማ በስተሰሜን ወደምትገኘውና ዩጋንዳንና ሩዋንዳን በሚያዋስነው አከባቢ ወዳለችው የM23 ጠንካራ ይዞታ ወደ ሆነው የሩትሹሩ ግዛት የጦር ትጥቅና የመድሃኒት አቅርቦቶቻቸውን ማጓጓዝ ጀምረዋል።


በኒውዮርክ የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ ሄርቬ ላድዞ አማጺያኑ ከከተማው መውጣት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል።

የM23 አማጺያን ከጎማ እንዲወጡ ከመወሰኑ በስተቀር የተኩስ አቁም ስምምነት እስካሁን አልተደረሰም። በሌላ በኩል የM23 አማጺያን የፖሊቲካ ዦን ማሪ ሩጋ ፣ የኮንጎ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ አማጺያኑ የጠየቁትን ሲያሟሉ ብቻ ከጎማ እንደሚወጡ ተናግረዋል፣


«ሚስተር ካቢላ በህዳር ወር ከተካሄደው ምርጫ በኋላ እስር ላይ ያሉትን ኤትዬን ቺሴኬዲን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ከእስር ይፍቱ እላለሁ። በሁለተኛ ደረጃ ሁሉም የፖሊቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንፈልጋለን። በቼበዬ ግድያ ጉዳይ የሚጠረጠሩ ጆን ሙምቢም እንዲታሰሩ እንፈልጋለን።

ጆን ሙምቢም የካቢላ ታማኝ ናቸው የሚባሉ የፖሊስ እንደራሴ ሲሆኑ፣ ቼባዬ ከተባሌው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግድያ ጋር በተያያዘ ይጠረጠራሉ። ኢትዬን ቺሴኬጂም ከወራት በፊት በኮንጎ በተደረገው ምርጫ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲን ወክለው ተወዳድረዋል። ነጻ መሆኑ በሚያጠራጥር ምርጫ ተቃናቃኛቸው ካቢላ አሸንፈዋል ቢባልም፣ ቺሴኬጂ ግን ራሳቸውን በራሳቸው አሸናፊ ነኝ ብለው አውጀው ነበር።
በኮንጎ ለተካሄዱ ግጭቶች ፍጻሜ ለማስገኘት እአአ በ2009 የተደረሱ ስምምነቶች ተፈጻሚ አልሆኑም በሚል ተቃውሞ ነበር የM23 አማጺ ቡድን ባሳለፍነው የፈረንጆች ሚያዚያ ወር ከዲሚክራያዊ ኮንጎ ጦር ተገንጥሎ የወጣው። በኮንጎ ውስጥ በየጊዜው የተቀሰቀሱ ግጭቶች ብዙ ሰዎችን ለህልፈተ ህይወት ቢዳርጉም፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እስካሁን በርግጥ ምን ያህል መሆኑ አይታወቅም።

ገመቹ በቀለ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ