1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

UNDP እና የየሃገራት የልማት ደረጃ፧

ማክሰኞ፣ ኅዳር 17 2000

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) የየሃገራቱን የልማት ዕድገት የሚመለከተውን ዘገባ፧ ዛሬ፧ ከሠንጠረዥ ጋር አቅርቧል። ሠንጠረዡ ካካተታቸው 177 አገሮች መካከል ኢትዮጵያ 169ኛ ደረጃ ላይ ነው የምትገኘው። ዝርዝሩን፧ ከተክሌ የኋላ.........

https://p.dw.com/p/E87U
እ ጎ አ በ 2006 ዓ ም፧ የተ.መ.ድ. በረሃብ ላይ የመዝመቻ መታሰቢያ ዕለት፧ ጀርመን ውስጥ በሃምበርግ እስታዲየም ሲታሰብ፧
እ ጎ አ በ 2006 ዓ ም፧ የተ.መ.ድ. በረሃብ ላይ የመዝመቻ መታሰቢያ ዕለት፧ ጀርመን ውስጥ በሃምበርግ እስታዲየም ሲታሰብ፧ምስል UN
ከ 17 ያህል አገሮች የተሟላ መረጃ ባለመቅረቡ፧ አገሮቹም በሠንጠረዡ አልተካተቱም። የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው፧ በአጠቃላይ ልማት፧ የአንደኛነቱን ደረጃ አይስላንድ፧ ለመያዝ በቅታለች። ሁለተኛ ኖርዌይ፧ ሦስተኛ አውስትሬሊያ፧ ዩ ኤስ አሜሪካ ደግሞ፧ የ አሥራ ሁለተኛነቱን ደረጃ ይዛለች። 177 ኛ ወይም የመጨረሻ ሲዬራ ሊዮን ስትሆን፧ ቻድ፧ 170 ኛ፧ ኢትዮጵያ ደግሞ 169ኛ ሆናለች። ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎና ቡሩንዲ፧ ኢትዮጵያን ቀድመው፧ 168 ኛና 167ኛ ለመሆን በቅተዋል። የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርኀ-ግብር (UNDP) ስላቀረበው ሠንጠረዥ፧ በጀኔቭ የዚሁ መሥሪያ ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ Cecile Molinier....
«በሠንጠረዥ 1 ፧ ያጤኑበት መጨረሻ ላይ የሚታየው ዝርዝር የሚያመላክተው፧ የዝርዝር ጥናቱን ምንጭ ነው። ምንጩም፧ በጠቅላላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነው። ለምሳሌ፧ የድርጅቱ የትምህርት የሳይንስና የባህል ክፍል(UNESCO) ለትምህርት፧ የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት WHO) ለጤና፧ የዓለም ባንክ ሠንጠረዥ፧ የየሃገራቱን ያልተጣራ ብሔራዊ ገቢ ይመለከታል። እነዚህ ናቸው ዋንኞቹ የምንጠቀምባቸው ምንጮች! ሠንጠረዡም፧ የሚዘጋጀው፧ ዋና መቀመጫው ኒው ዮርክ በሆነው በሰብአዊ ልማት-ነክ ጽህፈት ቤት በኩል ነው«።
ታዲያ መለኪያዎቹ ምንድን ናቸው?
«የሰብአዊ ልማትን ሠንጠረጅ በማውጣቱ ረገድ፧ መለኪያው፧ ከዝርዝሩ መገንዘብ እንደሚቻለው፧ በዛ ያሉ መመዘኛዎችን ያጠቃለለ ሲሆን፧ የሰብአዊ ልማት-አዘል ሠንጠረዥ እንደእውነቱ ከሆነ፧ የተለያዩ መመዘኛዎች አማካይ ውጤት ነው። የነፍስ ወከፍ የዕድሜ መጠን፧ የማንበብና መጻፍ ደረጃ፧ የአምራች ኃይልና የማምረቻ ተቋማት ንፅፅር፧ ያልተጣራ የነፍስ-ወከፍ ገቢ...እነዚህ ናቸው፧ ሠንጠረዡን ለማዘጋጀት ዋና-ዋና መለኪያዎች ሆነው የቀረቡት።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፧ በጎርጎሪዮሳዊው 2000 ዓመት በነደፈው የዓማአት የልማት ግብ ባለው አቅድ፧ በ አሥራ አምስት ዓመት ውስጥ፧ ድህነትን ጋማሽ-በግማሽ ለመቅረፍ፧ ማይምነትን ለማጥፋት፧ ህክምናን በሰፊው ለማዳረስ...እነዚህንና የመሳሰሉትን ተግባራት እንዲከናወኑ ይጠብቃል። የቀሩት ዓመታት አሁን ስምንት ገደማ መሆናቸው ነው። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሊሣካ ይችላል ወይ? «ሚስ« ሰሲል ሞሊንዬ+”....
«ከወራት በፊት፧ እቅዱ ግማሽ ዘመን እንደቀረው፧ የተባበሩት መንግሥታት ያሠፈረው ዘገባ፧ አዎንታዊ የሆነ፧ የሚያረካ፧ የሚያሳስብም ሁኔታዎች ተከሥተውበታል። አዎንታዊ ሂደት፧ ባጠቃላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድህነት እጅግ ተቀንሷል። ከአምሥት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ህጻናት በብዛት መሞታቸው ቀንሷል። የትምህርት ደረጃ ተሻሽሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያመረቃ ሂደት ነው የታየው። ይሁንና፧ አማካዩን የልማት ሂደት በተለይ በተናጠል በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለያዩ አገሮች ስንመለከት፧ ያሳዝናል፧ ብዙዎቹ፧ የዓማአቱን ግብ ማሣካት የሚችሉ አይደሉም። ስለሆነም፧ ዋናው መልእክታችን፧ የዓማአቱ ግቦች፧ ሁሉንም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል መንግሥታት የልማት ድርጅቶችን በመላ የሚመለከቱ ናቸው። መመሪያዎቹን የሚከተሉ ከሆነ፧ ይፋ የልማት እርዳታ በርከት ካለ፧ በተለይ፧ እጅግ ለደኸዩት አገሮች ላቅ ያለ ትኩረት ከተሰጠ፧ እነርሱም ያላቸውን ጥሬ የሀብት ምንጭ በተገቢው ቦታ ካዋሉ እቅዱ፧ ግቡን ሊመታ ይችላል። ነገር ግን፧ አያሌ አገሮች፧ ከድህነት ወጥመድ ውስጥ እንደገቡ ናቸው። ሀብታቸውን፧ በተገቢው የልኣም ዘርፍ እንዲውል ካላደረጉ ለሰብአዊ ልማት የሚገባውን ለማድረግ ካልጣሩ፧ የዕድገት ጮራ ሊያዩ አይችሉም። ቀቢጸ-ተስፋ የሚያሳድር አይደለም። ማበረታታት ነው የሚገባን! የልኣም እንቅሥቃሤአቸውን በጥሞና የምንከታተለውም፧ አዎንታዊ እመርታን፧ የቀረውንና ሊደረስበት የሚገባውንም ሩቅ ግብ ለማሳየት ነው።«