1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

ሂሳብና ስታስቲክስ ለሳይንስ ያለው ሚና

ረቡዕ፣ የካቲት 13 2011

የሂሳብና የስታስቲክስ የትምህርት ዘርፎች ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት የጀርባ አጥንት ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡ እነኝህ የዕውቀት ዘርፎች የሰው ልጅ እስከዛሬ ሲሰራባቸው የቆዩ የአመራረት ሂደቶችን/ በአዳዲስ ዘዴዎች በመተካትና በማስተዋወቅ ለኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ዕድገት መፋጠን ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ይታወቃል፡፡

https://p.dw.com/p/3Dkc0
Diskussion über die Rolle von Mathematik und Statistik für Wissenschaft und Technologie: Hawassa Universität 20.02.2019
ምስል DW/S. Wegayehu

ሒሳብና ስታትስቲክስ ለሳይንስ

በተለይም የአዳጊ አጋርትን ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ / በእነኝሁ የትምህርት ዘርፎች የሰለጠኑ ባለሙያዎች መኖር ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በዚህ ረገድ ታዲያ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲው በሂሳብና ስታስቲክስ ሳይንስ ትምህርት መስክ የሰለጠነ የሰው ሐይል ለማፍራት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተለይም ካለፉት አሥር ዓመታት ወዲህ በኖርዌይ አገር ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በነደፈው  የጋራ ፕሮጀክት  በዘርፉ የሚታየው የሠለጠነ የሰው ኃይል አጥረት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ለማቃለል አንዳስቻለው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ይገልጻሉ፡፡
የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለመገምገምና  በሂሳብ ሳይንስ ዘርፍ የሌሎች አገራት ልምዶችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባዔ እዚህ ሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ዘይቱ ጋሻው ዩኒቨርሲቲው እያካሄደ የሚገኘው የጋራ ፕሮጀክት  በአገር አቀፍ ደረጃ ብቃት ያላቸው የሂሳብና የስታስቲክስ ባለሙያዎችን ለማፍራት ከፍተኛ አገዛ ማድረጉን ይናገራሉ ፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብና ስታስቲክስ ዘርፍ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው ፕሮጀክት  በዘርፉ የሠለጠኑ ባለሙያዎችን በማፍራት ብቻ የተገደበ አለመሆኑ በምርምር ጉባኤው ላይ ተገልቷል።
በተለይም በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ለተገነቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት / የድህረ ምረቃ ሥረዓተ ትምህርቱን በማጋራትና በማስተዋወቅ  በዘርፉ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን እንዲጀምሩና እንዲያስፋፉ የራሱን ድጋፍና አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡

Diskussion über die Rolle von Mathematik und Statistik für Wissenschaft und Technologie: Hawassa Universität 20.02.2019
ምስል DW/S. Wegayehu

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ