1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዳዋ ኹከትና ኢሕአዴግ

ማክሰኞ፣ ጥር 21 2011

ዘመናይቱ ከተማ ለበርካታ ዓመታት የምትገዛዉ የምክር ቤቷን መቀመጫ 40-40-20 በሚል በተቀራመቱት በኢሕአዴግና የኢሕአዴግ አጋር በመሆነዉ በኢሶሕዴፓ ነዉ።የጥምቀትን በዓል እንደብሶት መግለጫ የተጠቀሙበት የከተማይቱ ወጣቶች ከተማይቱ የምትገዛበት ክፍፍል እንዲለወጥ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3COF3
Äthiopien Dire Dawa - Unruhen
ምስል DW/M. Teklu

(Beri.DD) Dire Dawa-Unrest - MP3-Stereo

የድሬዳዋ ከተማን ያበጠዉ ግጭትና ሁከት መሠረታዊ መንስኤ የከተማይቱ አስተዳደር የሕዝቡን ፍላጎት ማርካት ባለመቻሉ እንደሆነ የከተማይቱ ዋነኛ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ አመነ።ዘመናይቱ ከተማ ለበርካታ ዓመታት የምትገዛዉ የምክር ቤቷን መቀመጫ 40-40-20 በሚል በተቀራመቱት በኢሕአዴግና የኢሕአዴግ አጋር በመሆነዉ በኢሶሕዴፓ ነዉ።የጥምቀትን በዓል እንደብሶት መግለጫ የተጠቀሙበት የከተማይቱ ወጣቶች ከተማይቱ የምትገዛበት ክፍፍል እንዲለወጥ ጠይቀዋል።ከመቶዎቹ መቆመጫዎች 60ዉን የሚቆጣጠረዉ የከተማይቱ ኢሕአዴግ ፅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከበደ ፓርቲያቸዉ የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ አለመቻሉን አምነዋል፣ይቅርታ ጠይቀዋልም።

መሳይ ተክሉ  

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ