1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ሕክምና ቅዱስ ነው አታርክሱት» ተቃውሞ የወጡ ተለማማጅ ሐኪሞች

ሰኞ፣ ሚያዝያ 14 2011

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ "ሙያችን ይከበር፤ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ንቃ" ሲሉ ተደምጠዋል። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ከሚያዝያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ተቋማት ውይይት እንደሚደረግ አስታውቋል

https://p.dw.com/p/3HELM
Äthiopien - Krankenhausmitabeiter protestieren in Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

ተለማማጅ የሕክምና ባለሙያዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ከሙያቸው ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳት ዛሬ ተቃውሞ አደረጉ። ተማሪዎቹ ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ያሰሙት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ነው። 
ተማሪዎቹ በተቃውሞ ላይ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል «የሚከፈለን እና የምንሠራው ተመጣጣኝ ይሁን» ፣ «ሥራ እንፈልጋለን» የሚሉ ይገኙበታል። “በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚደርስን ማዋከብ እንቃወማለን” ያሉት ተማሪዎቹ “የህክምና ሙያ ይከበር” ሲሉ አሳስበዋል። በተማሪዎች ላይ ከሚደርሱ ችግሮች በተጨማሪም በአጠቃላይ ”የጤና ዘርፉ ለውጥ እንደሚያሻውም” ጠቁመዋል። 
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማምሻውን «ሰሞኑን በአንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የህክምና ትምህርት ተማሪዎቻችን ያነሷቸውን ጥያቄዎች በጥሞና በማጤን በተነሱት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከነገ ሚያዝያ 15 ቀን 2011 ዓ ም ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ተቋማት ውይይት የሚካሄድ መሆኑን እንገልጻለን» ብሏል።

ሰለሞን ሙጬ

እሸቴ በቀለ

ተስፋለም ወልደየስ