1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2011

ኢትዮጵያ  ባለፉት ሦስት ዓመታት ከመንፈቅ በሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ማለትም ኮንትሮባንድ ምክንያት ከ 14 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቷ ተነገረ። በሀገሪቱ አስላጊው የጉምሩክ ስነስርአት ሳይፈጸምባቸው ወደሀገር ውስጥ የሚገቡም ይሁን የሚወጡ ሸቀጦች መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

https://p.dw.com/p/3AG7R
Äthiopien Notstände in Amhara
ምስል DW/J. Jeffrey

«ኢትዮጵያን ከ 14 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አሳጥቷል»

 ለችግሩ መባባስ ሕገወጥ የጥቅም ትስስር፤ በሀገሪቱ የሚታየው ግጭትና አለመረጋጋት፤ ጠንካራ ሕግን የማስከበር ሥራ አለመኖር እና የኅብረተሰቡ ቸልተኝነት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች ፡ ምሥራቅ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ችግሩ በስፋት የሚታይባቸው አካባቢዎች ሲሆኑ ፡ የቅባት እህሎች ፡ የቀንድ ከብት እና የመሳሰሉት ከኢትዮጵያ ሲወጡ ፡ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች ፡ የታሸጉ ምግቦች ፡ ሃሽሽ ፡የጦር መሣሪያ፡ የመዋቢያ ቁሳቁሶች እና ሞተር ሳይክልን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡ ታውቋል። ድርጊቱ ከጥቅም ተጋሪዎች እና ከአንዳንድ የመንግሥት አካላት ሳይቀር ሽፋን እና ከለላ እንደሚደረግለት ነው የተገለጸው ። መንግሥት በተለያዩ የሀገሪቱ ጠረፍ አካባቢዎች ተመሳሳይ ባህል፣ ወግ እና አኗኗር ላላቸው የጎረቤት ሃገራት ህዝቦች የፈቀደው ፍራንኮ ቫሎታ  “ የተሰኘ የነጻ የመሠረታዊ ሸቀጦች ግብይት አላማውን ስቶ ለሕገ ወጥ ንግድ መጋለጡ ለችግሩ መባባስ ሌላኛው ምክንያት ሆኖ ተቀምጧል።  ኮንትሮባንድ ሕጋዊ ነጋዴዎች ላይም  ከፍተኛ አሉታዊ  ጫና እያሳረፈ ከመቀነስ ይልቅ እየተባባሰ መሄዱ ን የገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። ይህንንም ተከትሎ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ የሚሆን የጉምሩክ ፖሊስ እንዲደራጅ ውሳኔ ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡

ሰለሞን ሙጨ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ