1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መለስተኛ የደጋፊዎች ግጭት በአዲስ አበባ ስታዲየም

ማክሰኞ፣ ሰኔ 11 2011

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ሲለያዩ ደጋፊዎች አላስፈላጊ ምልክቶችን በማሳየት ከጨዋታው በፊትም መጠነኛ ግጭት መከሰቱ ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/3Keel
Fussball Symbolbild - Tor
ምስል picture-alliance/dpa/J. Woitas

ከስታዲየም ውጪ መጠነኛ ግጭት ታይቷል

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ሲለያዩ ደጋፊዎች አላስፈላጊ ምልክቶችን በማሳየት ከጨዋታው በፊትም መጠነኛ ግጭት መከሰቱ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ ከዚህ ቀደም በጸጥታ ስጋት የተነሳ ተሰርዞ የፕሬሚየር ሊጉም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተደርጎ ነበር። የዛሬውን ጨዋታ ኦምና ታደለ ስታዲየም በመገኘት ተከታትሏል። ስቱዲዮ ከመግባታችን ጥቂት ቀደም ብሎ በስልክ ቃለ መጠይቅ አድርገንለታል። የጸጥታ ሁኔታው ዛሬ በስታዲየም እና ከስታዲየም ውጪ ምን ይመስል ነበር? ፕሬሚየር ሊጉ እንዲቋረጥ ያደረገው የጸጥታ ስጋታስ በተወሰነ መልኩ ይታይ እንደነበር በመግለጥ የተመለከተውን ያካፍለናል። 

ኦምና ታደለ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ