1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መፍትሄ የሚሻው የሰላም ጉዳይ

እሑድ፣ ኅዳር 30 2011

በአዲስ የለውጥ ሂደት ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩት አለመረጋጋቶች የሀገሪቱን ሰላም ስጋት ላይ እንደጣሉት ነው የሚነገረው። ግጭቱ በሚታይባቸው አካባቢዎች የሚጠፋው የሰው ሕይወት፤ የሚወድመው ንብረትም ሆነ የዜጎች መፈናቀል እየተወገዘ መንግሥት ላለመረጋጋቱ የመፍትሄ ርምጃ ለመውሰድ ዘግይቷል በሚል ይቀሳል።

https://p.dw.com/p/39giG
Karte Äthiopien AM

«ሰላምን ለማስፈን ወደራሳችን እንመለስ»

 መንግሥት በበኩሉ ሰላምን የሚያውኩ የተደራጁ ኃይሎች መኖራቸውን በመጥቀስ የግጭቱ ለኳሾች ናቸው ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማድረግ መጀመሩን ይገልጻል። የሰላም መደፍረስ ያሰጋቸው ዜጎች የሰላም ጥሪን ከክልል ክልል እየተዘዋወሩ እያቀርባሉ። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ራሱ ገዢው ፓርቲ በውስጡ የተፈጠረው መቃቃር፤ የሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር እና ለውጡ ያልተመቻቸው ኃይሎችን በምክንያትነት ያነሳሉ። የሰላም እና ብሔራዊ እርቅ አስፈላጊነት በሚነገርባት ሀገር እውነተኛ ሰላም ለማውረድ ለምን ጊዜ ወሰደ? የሚሉ ነጥቦችን በማንሳት የተካሄደውን ውይይት ከድምጽ ቅንብሩ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ