1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምክር ቤት የምሕረት አዋጁን አጸደቀ

ዓርብ፣ ሐምሌ 13 2010

የተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ። በስብሰባውም ሲጠበቅ የነበረው እና በተለያየ የወንጀል ድርጊት ለተሳተፉ ሰዎች ምሕረት ለመስጠት የቀረበው ረቂቅ የምሕረት አዋጅ ፤ አዋጅ ቁጥር 1096ን አጽድቋል።

https://p.dw.com/p/31ph6
Das äthiopische Parlament
ምስል DW/G. Tedla

ለኢትዮጵያ ፕረስ ኤጀንሲም የቦርድ አባላትን ሰየመ

አዋጁ በአብላጫ የድጋፍ እና በአንድ ድምፀ ተአቅቦ መጽደቁ ነው  የተነገረው። ከዚህም ሌላ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅትን እንደገና ለማደራጀት የወጣውን አዋጅም አጽድቋል። ለፕረስ ድርጅቱም ስምንት ሰዎችን በቦርድ አባልነት ቃለ መሐላ ማስፈፀሙን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ