1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምግብና ማንነትን ያጣመረዉ የአራውሎ ምግብ ቤት

ዓርብ፣ ነሐሴ 11 2010

ምግብ እስከ ምን ድረስ ማንነትን ይገልፃል? እንዴትስ ከሰዉ ልጅ ሥር-ወመሰረት ጋር ዳግም እንድገናኝ ይረዳል? አንድ ሰዉ በልጅነት ዘመኑ የበላዉ የሚወደዉ ምግብ አለያም አያቶቹ ያበሉት በመጡበት አከባቢ የተለመደ ምግብ ከመጣበት አካባቢ ጋር የሚያቆራኝ ስሜት እንዲፈጠርበት ይረዳል።

https://p.dw.com/p/33HkB
Somalische Essen
ምስል DW/E. Wallis

ምግብና ማንነትን ያጣመረዉ የአራውሎ ምግብ ቤት

ፎዝያ እስማይል በብሪስቶል ውስጥ ኮረብታማ ግን ቅጠላማ በሆነዉ ቦታ ላይ አራዌሎ ኢትስ የሚባለው የሶማሌ ምግብ ቤት ባለቤት ነኝ ። በምግብ ቤቱ ዉስጥም ፎዝያና ባለቤቷ አንድይ ይገኛሉ። አንድይ ምግብ በማብሰልና ምሽቱን እንግዳ በመቀበል ፎዝያን ይረዳታል። አራዌሎ ምግብ ቤትን ለማቋቋም ያነሳሳቸዉ ዋናው ምክንያት ከሶማሌ ሥረ-መሠረትዋ ጋር ለመገናኘት ፍላጎት ስለነበራት ነዉ። ፎዝያ ይህን ምግብ ቤት ለማቋቋም ያነሳሳትን ምክንያት እንደምከተለዉ ታብራራለች፣ «እዉነቱን ለመናገር በብሪግዚት ህዝበ ውሳኔ እና በነበረው የጥላቻ ድባብ  እኔ ባህሌን እንደገና ለመማር ስለፈለኩና በምግብ አማካይነት ከባሕሌ ጋር ዳግም ስለፈለኩ ነዉ። እሄ ነዉ በኢዉነቱ ያነሳሳኝ። ለንዳን ነዉ ያደኩት። ቤቴሴቦችም አሁንም እዛ ነዉ ያሉት። ብርስቶል ኑሮዬን ሳደርግ በጣም የናፍቀኝ ነገር ካለ  የሶማሊ ምግብ ነዉ። ምክንያቱም እውነቱን ለመናገር እናቴ ስላለች እኔ እምብዛም ምግብ አብስዬ አላዉቅም። ስለዚህ በምንም መንገድ ምግብ ማብሰል መማር ነበረብኝ።»

አራዌሎ ምግብ ቤት የሚለው ስም የመጣው ከሶማሊያ ጥንታዊ ንግሥት ታሪክ ነዉ። ንግስቷም የምትታወቀዉ ሴቶች በማህበረሰቡ ዉስጥ ጠንካራ ሚና እንዲኖራቸዉ በማድረግና ሶማሊያን በሴቶች በሚመራ ስርዓት በማስተዳደር ነዉ። በአንድ ታሪኮች ዉስጥ የተሳለችዉ ወንዶችን በማኮላሸት ነዉ። ግን ለፎዝያ ጠቃሚዉ ነገር ንግስቷ በስልጣን ዘመኗ የወደፊት ጉዞዋን ያመቻችበት ሁኔታ ነዉ። ይህ ደግሞ ከፎዝያና ከእናቷ ጋር በትንሹ ይመሳሰላል። ፎዝያ:«እናቴ የምትደነቅ ባለሞያ ናት። ግን አልተማረችም። ያደገችዉ በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ ድንበር ላይ እንደ አርብቶ አደር ነዉ። ከሶማሌላንድ ወደ ኩዌት ከተሰደደች በኋላ ብዙ የምግብ አይነቶችን የማወቅ እድል ሰጥቷታል። ትምህርት ባይኖራትም ስለ ምግብ ብዙ አስተምራናለች።»

Somalische Essen Fozia Ismail
ፎዝያ እስማይልምስል DW/E. Wallis

አሁን በተራዋ ፎዝያ እንግዶቿን በምግብ ብዙ ታስተምራለች። በአራዌሎ ምግብ ቤት ለተገኙት ለ14 እንግዳዎች በሙሉ ምግቧን ታስተዋዉቃለች። እንግዶቿም ምግብ እስከሚዘጋጅ ድረስ ከፎዝያ ጋር ከምግቡ ጋር ይተዋወቃሉ። የፎዝያ እናት እሷን ጨምሮ 10 ልጆች አላቸዉ። የፎዝያ እናት ከባላቸዉ ጋር የነበራቸዉ ግኑኝነት አስቸጋር ስለነበረ እንደ አዉሮጳዎቹ አቆጣጠር በ1985 10 ልጆቻቸዉን ወደ ታላቋ ብርታንያ ለመኖር መጡ። ፎዝያ: «ቤቴሰቦቼ ትልቅ ናቸዉ። አምስት ወንድምና አራት እህት አሉኝ። ብዙ ሰዎችን ነዉ የምትመግበዉ። ይሁን እንጅ በጣም ዘና የምትለዉ ምግብ ለማብሰል ማዓድ-ቤት ስትገኝ ነዉ። እኔ  ምንም የምግብ አሰራር አልተማርኩም ነበር። ላሆ የሚባለዉን፣ ከኢትዮጵያ እንጀራ ጋር የሚመሳሰል፣ እንዴት እንደሚሰራ ለመማር እወድ ነበር። አሁንም ላሆ እንደት እንደሚሰራ መማር አለብኝ።»

ፎዝያ በካምብርጅ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ አንትሮፖሎጂ ነዉ ያጠናቸዉ። በትምህርት ቆይታዋ ደስተኛ ናት። ግን እንደ አንድ ሶማሊያዊ ሴት ልዩ እንክብካቤ ከሚደረግላቸዉ ሃብታም ነጮች ጋር መማር አስቸጋሪ እንደነበረ ትናገራለች። ፎዝያ: «ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ለመግባት የነበረኝ ፉክክር ያስደስተኛል። ግን ዩኒቨርሲቲዉ ከእዉነታ የራቀ ነዉ። ምክንያቱም በጣም ሃብታም የሆኑ የነጮች ልጆች ስለ ዓለም ያላቸዉ ሃሳብ ዉስን ነዉ።  እንደ አንድ የሶማሊያ ሴት ማኅበራዊ አንትሮፖሎጂን እዛ በመማሬ ጥሩ ስሜት አልተሰማኝም። ግን እንዳነብ ፍላጎት አሳድሮብኛል። ስለ ዓለም ምግብ እንዳሰላስልም እድል ሰጥቶኛል።»

ፎዚያ ምግብንና የማንነት ፖለትካ በተመለከተ በኦክስፎር ሲይምፖስያም ላይ ወረቀት አቅርባለች። አሉ የምባሉ ምግብ ቤቶችም በነጮች ቁጥጥር ስር እንዳለም ፎዝያ ትናገራለች። ፎዝያ: «ምግብ፣ ጉዞና ሃብታምነት መገናኘቱ አንዳንዴ ያናድደኛል። በአለም ላይ የምጓዙት ሃብታም ነጮች፤ አድስ ምግብን አገኘን የምሉት ሃብታም ነጮች። አድስ ምግብ  የምባል ነገር የለም። ምግብ ከጅሚሩም ያለ ነዉ። እሄንን ነዉ እኔ እጅግ አጸያፊ ሆኖ ያገኘዉት።»

Somalische Essen
ምስል DW/E. Wallis

የሶማሊያ ምግብና ማንነት ከንግድና ከቅኝ-ግዛት ጋርም የተቆራኘ ነዉ። ለምሳሌ ፓስታ ከጣልያን፣ ሳምቡሳ ከሕንድና ከመካከለኛዉ ምስራቅ እንደመጣ ፎዝያ ትናገራለች። ይሁን እንጅ የሰማሊ ባህል ነዉ ለፎዝያ  ቦታ ያለዉ። ይህንንም ከአፍርቃዊ ሥር-መሰረት ጋር ታገናኛለች። ፎዝያ: «እንደሚመስለኝ ብዙ ሶማሌዎች ከጥቁርነታቸዉ ጋር ዳግም ለማጣመር ላይ ኢየሞከሩ ነዉ። እኔ ሁሌም ራሴን እንደ ጥቁር-ብሪታናዊ-ሶማሌ አርጌ ነዉ የማያዉ። ሌሎች  ማንነታቸዉን ከአፍሪቃ ጋር ማጣመር አይፈልጉም፣ ይልቁንስ ከአረብ ባሕል ጋር እንጅ። ግን ብዙ የሶማሌ ወጣቶች ስለ ራሳቸው ባህልና ቅድመ-እስልምና ታሪክ ዳግም እየተማሩ ነዉ።»

ፎዝያ ባህሏን ስትዳስስ እንግዳ ተቀባይነትና ለእንግዳ ምግብ ማብሰል አንዱ ሆኖ ታገኛለች። ለምሳሌ ሰዎችን ወደ ቤት ጋብዞ ለነሱ ምግብ ማብሰል። ፎዝያ: «የእንግዳ ተቀባይነት ሃሳብ  እወደዋለዉ። ይህም ለአርብቶ አደር ማህበረሰብ በጣም አሰፈላጊ ነዉ። ምክንያቱም መጥፎ ጊዜ ስያጋጥም ጎሮቤቶችህ ይረዳሉ። ሁሉም ሶማሊያዊ ሲያድግ ከዚህ የእንግዳ አቀባበል ሃሳብ ጋር ነዉ የሚያድገዉ። ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ይመስለኛል።

ኤማ ዋልስ

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ