1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰማያዊ ፓርቲ መክሰሙ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 22 2011

ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ጋር በመጣመር ታላቅ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመሥረት ያስችለውን ዘንድ ራሱን ማክሰሙን ይፋ አደረገ። ፓርቲው በሀገሪቱ አዲስ ያለውን ርምጃ የወሰነው እሁድ ታኅሣስ 21 ቀን 2011ዓ,ም ባካሄደው የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው። ውሳኔውም በአራት ድምፀ ተአቅቦ እና አንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ማለፉንም አመልክቷል።

https://p.dw.com/p/3Ap7l
Äthiopien - Blue Party Pressekonferenz: Ato Abebe Akalu PR, Ato Yeshiwas Asefa und Ato Getahun Balcha
ምስል DW/Y. G. Egiyiabher

«ውሳኔው በአራት ድምፀ ተአቅቦ እና አንድ ተቃውሞ አልፏል»

እስካሁን ከግንቦት ሰባት፣ ኢዴፓ እና እነ አቶ አንዷለን አራጌ ከመሳሰሉ ፖለቲከኞች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፓርቲው የቀድሞ ኃላፊዎች ዛሬ ከቀትር በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ትናንት ፓርቲው ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው እንደሆነም አመልክተዋል። መግለጫውን የተከታተለው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ