1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳይታወቅ ሕይወት ቀጣፊው ሄፓታይተስ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2010

ሄፓታይተስ ቢ ወይም ሲ በመባል የሚታወቀዉ የጤና እክል በመላው ዓለም በየዓመቱ ከ1, ሚሊየን የሚበልጥ ሕዝብ ምክንያት መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። የበሽታው ልዩ ባህርይ ሰዎች በዚህ ህመም መያዛቸውን ሳያውቅ ለረዥም ዓመታት ተደብቆ መቆየቱ ነው።

https://p.dw.com/p/32OxT
Hepatitis B Virus Viren
ምስል Creative Commons/Wikipedia

ሳይታወቅ ሕይወት ቀጣፊው ሄፓታይተስ

በመላው ዓለም 325 ሚሊየን ሕዝብ በሄፓታይተስ ቢ ወይም ሲ በመባል ለሚታወቀው የጤና እክል መጋለጡን የዓለም የጤና ድርጅት ይገልጻል። ከተጠቀሰው ቁጥር 290 ሚሊየን የሚሆነው ደግሞ በዚህ በሽታ መያዙን ሳያውቅ የሚኖር መሆኑንም ድርጅቱ አመልክቷል። ሄፓታይተስ በሚል ከኤ እስከ ኢ ድረስ እንደሚዘረዘር ይህ ሁሉ ግን ከጉብት ጋር የሚገናኝ ህመም መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በሽታው ተሰውሮ የብዙ ሰዎች ሕይወት እንደሚጎዳ በመታወቁም በየዓመቱ በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ሐምሌ 28 ሰዎች ስለበሽታው ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማስተማሪያ እና የማሳሰቢያ ዕለት እንዲሆን የዛሬ ስምንት ዓመት የዓለም የጤና ጉባኤ ላይ ተወሰነ። ዶክተር ሊበን በሽር በጀርመን ሙኒክ ከተማ በግላቸው ክኒሊክ አገልግሎት የሚሰጡ አጠቃላይ እና የውስጥ ደዌ ሀኪም ናቸው። ዶክተር ሊበን እንደሚሉት ከሄፓታይተስ ኤ ጀምሮ እስከ ኢ አምስት አንዳንዴም እስከ ስድስት ሊሄድ ይችላል የቫይረሱ አይነት። ምንነታቸውን እና የሚያደርሱትን ጉዳት እንዲህ ይዘረዝሩታል። ሲጋራ የሳንባ ካንሰርን እንደሚያስከትል ሁሉ ሄፓታይተስም በዋናነት የጉበት ካንሰርን ሊያስከትል እንደሚችል የህክምና ባለሙያው ገልጸዋል። በዓለም ላይም የሞት መጠን ሲታይ ከሳንባ ካንሰር ቀጥሎ በጉበት ካንሰር የሚሞተው ከፍተኛ ቁጥር እንዳለውም ጠቁመዋል። ሄፓታይተስ ቢ ወይም ሲ ሲባል እንሰማለን፤ እንዴት አይነት በሽታ ነው? ስንል ጠይቀናል። የሰጡትን ሰፊ ማብራሪያ ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ