ስደት በስደተኞች በጥበብ ሲገለጽ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 19 2011ማስታወቂያ
ስደተኞች ስለስደት ጉዟቸው ጥበባዊ በሆነ መልኩ የሚገልፁበት የጥበብ ትዕይንት በፈረንሳይዋ የዲጆ ከተማ በሚገኘው የዲጆ ረቂቅ ጥበብ ቤተመዘክር ውስጥ ለጎብኝዎች ሰሞኑን ይፋ የሆነው። የተገን ጠያቂዎች ማረፊያ ማዕከል ወይማ ካዳ ተብሎ በምህጻሩ በሚታወቀው ተቋም ውስጥ ይገኙ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች ሃገራት ተሰዳጆችም በዲጆ ከሚገኙ የፈረንሳይ የጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ነው በአንድ ላይ ሥራቸውን ለተመልካች ያቀረቡት። ትርዒቱ ስደተኞቹ በመረጧቸው የጥበብ የሥዕል ሥራዎች ላይ በስነጽሑፍ እና በሙዚቃ ተቀነባብሮ የቀረበ ሲሆን በተመልካቹም ዘንድ ስሜትን በመንካት ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱም ተነግሯል። ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ