1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሞስኮ የሩስያ የንግድ ሚኒስትሮች ሌላ የድሮን ጥቃት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 25 2015

የሩስያ ዋና መዲና ሞስኮ እንደገና የአንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ኢላማ ሆነ። ጥቃቱ ለሁለተኛ ጊዜ በሦስት ቀናት ዉስጥ የተፈፀመዉ የሩስያ የንግድ ሚኒስትር መሥርያ ቤቶች በሚገኙበት ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ ላይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/4Uehb
Moskau Drohnenangriff auf Hochhaus
ምስል EVGENIA NOVOZHENINA/REUTERS

የሩስያ ዋና መዲና ሞስኮ እንደገና የአንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ኢላማ ሆነ። ጥቃቱ ለሁለተኛ ጊዜ በሦስት ቀናት ዉስጥ የተፈፀመዉ የሩስያ የንግድ ሚኒስትር መሥርያ ቤቶች በሚገኙበት ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ ላይ ነዉ። በሌላ በኩል የሩስያ ፀረ-አውሮፕላን መከላከያዎች በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸዉን የሞስኮ ከተማ  ከንቲባ ሰርጌይ ሶቢያኒን ተናግረዋል። ሞስኮ ጥቃቱን የዩክሬይ የሽብር ጥቃት ብሎታል። በጥቃቱ የሕንጻዉ 21 ኛው ፎቅ የፊት ለፊት ገፅታ ተጎድቷል፤ በ 150 ካሬ ሜትር ቦታን የሚሸፍን ቦታም መዉደሙ ተዘግቧል።  የሩስያ የዜና ወኪል ታስ TASS የሩስያን የመከላከያ ሚኒስቴር ጠቅሶ እንደዘገበዉ ጥቃት የጣሉት የሰው አልባ አውሮፕላኖች የዩክሬን ናቸዉ። የዩክሬይን ፕሬዝዳንት አማካሪ በበኩላቸዉ ሞስኮ ተጨማሪ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃቶች እንደሚደርሱባት ልታዉቅ ይገባል ማለታቸዉ ተዘግቧል።  

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ