1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የሕጻናት ጋብቻ

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2011

የትግራይ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ እንደሚገልፀው ባለፊት 6 ወራት 407 ሴት ህፃናት ለመዳር ተዘጋጅተው ነበር፡፡ ከነዚህ እስካሁን የተዳሩት ሰባት ናቸው፡፡ ከ400ዎቹ የ38ቱ በመንግስትና በሕብረተሰብ ጥረት መቅረቱን የትግራይ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡ የተቀሩት ደግሞ እንዳይፈፀሙ የተለያዩ ተግባራት እየተከወነ መሆኑ ቢሮው ይገልፃል፡፡

https://p.dw.com/p/3Cj1r
kleine Mädchen in einer Schule in Tigray
ምስል DW

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሕፃናት ጋብቻ እየቀነሰ መምጣቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ በተለይም በጥር ወር በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ፣ሴቶች ለአቅመ ሄዋን ሳይደርሱ በወላጆቻቸው ግፊት እንዳይዳሩ ከፍተኛ ክትትል እንደሚደረግ ተገልፅዋል፡፡ እስከ 2017 ዓመተ ምህረት የሕፃናት ጋብቻ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረትም እየተሰራ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ሕፃናት ድርጅት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ከሆኑ አምስት ህፃናት መካከል አንድዋ ትዳራለች፡፡ ይህ አሃዝ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ከአራት ልጆች አንዷ እንደነበር ድርጅቱ ይገልፃል፡፡ በኢትዮጵያ የሕፃናት ጋብቻ በአንድ ሶስተኛ መቀነሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይሁንና አሁንም ተጨማሪ ስራ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል፡፡

የትግራይ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ እንደሚገልፀው ባለፊት ስድስት ወራት 407 ሴት ህፃናት ለመዳር ተዘጋጅተው ነበር፡፡ ከነዚህ እስካሁን የተዳሩት ሰባት ናቸው፡፡ ከአራት መቶዎቹ የ38ቱ በመንግስትና ሕብረተሰብ ጥረት እንዲቀር መደረጉ የትግራይ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡ የተቀሩት ደግሞ እንዳይፈፀሙ የተለያዩ ተግባራት እየተከወነ መሆኑ ቢሮው ይገልፃል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ግን በክልሉ የሕፃናት ጋብቻ በከፍተኛ መጠን መቀነሱ የትግራይ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሐላፊዋ ዶክተር የትምወርቅ ገብረመስቀል ለDW ተናግረዋል።

መጠኑ እንዲቀንስ የሃይማኖት መሪዎችና ሀገር ሽማግሌዋች ጥረት ከፍተኛ እንደሆነም ተገልፃል፡፡ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ግለሰቦችም በጉዳዩ ላይ እየሰሩ መሆኑ ተገልፃል፡፡

kleine Mädchen in einer Schule in Tigray
ምስል DW

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ኂሩት መለሰ