1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት

ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2011

በትግራይ የኢንቨስትመንት ፍሰት እያደገ መምጣቱ የክልሉ መንግስትና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ይገልፃሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የጀመረችው አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ ማደግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ባለሀብቶችና የኢኮኖሚ ምሁራን ይናገራሉ፡፡

https://p.dw.com/p/3KIIg
Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie

የኢንቨስትመንት መርህ የያዘ መንግስት ለኢንቨስተሮች የተሻለ መተማመን ይፈጥራል


በትግራይ የኢንቨስትመንት ፍሰት እያደገ መምጣቱ የክልሉ መንግስትና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ይገልፃሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የጀመረችው አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ ማደግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ባለሀብቶችና የኢኮኖሚ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ የትግራይ ክልል መንግስት በበኩሉ የተፈጠረው ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድል ለመጠቀም እየሰራሁ ነው ይላል፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመቐለ ከተማ ብቻ 170 የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች ከ13 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ፋብሪካዎች ለመገንባት ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል። 
በትግራይ የኢንቨስትመንት ፍሰት እያደገ መምጣቱ የክልሉ መንግስትና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ይገልፃሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የጀመረችው አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ ማደግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ባለሀብቶችና የኢኮኖሚ ምሁራን ይናገራሉ። የትግራይ ክልል መንግስት በበኩሉ የተፈጠረው ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድል ለመጠቀም እየሰራሁ ነው ይላል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመቐለ ከተማ ብቻ 170 የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች ከ13 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ፋብሪካዎች ለመገንባት ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል። 
የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ትእምት) መዋዕለ ነዋዩ ከሚያፈስባቸው ስራዎች ውጪ ሌሎች ትላልቅ ኢንቨስትመንቶች የሚጠበቀውን ያክል አይታይባትም የምትባለው ትግራይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የተሻለ የኢንቨስትመንት ፍሰት እያስተናገደች መሆኑ ይገለፃል። በተለይም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ በክልሉ ኢንቨስትመንት የማድረግ ፍላጎት በከፍተኛ መጠን ማደጉ የሚጠቀስ ሲሆን፣ የያለፉት ዘጠኝ ወራት ሪፖርትም ይህንኑ እንደሚያሳይ በኢኮኖሚ ዘርፍ የሚሰሩ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ።  እንደ ትግራይ ክልል ንግድ ኢንዳስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ገለፃ ባለፉት ዘጠኝ ወረት ብቻ በትግራይ ኢንቨስት ለማድረግ የጠየቁ 1258 ኢንቨስተሮች ያላቸው አቅም ታይቶ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል ይላል። ባለሀብቶቹ በድምር 38 ቢልዮን ብር ገደማ ካፒታል ማስመዝገባቸው የቢሮው ሪፖርት ያመለክታል። ይህም ካለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ግዜ ጋር ሲነፃፀር የኢንቨስትመንት ፍሰቱ በእጥፍ ማደጉ እንደሚያመለክት የትግራይ ክልል ንግድ፣ ኢንዳስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ  የኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀፍቶም ፈንታሁን የሰጡን መረጃ ያስረዳል። ኮንስትራክሽን፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ሆቴልና ቱሪዝም፣ ግብርናና መአድን ዘርፎች በኢንቨስተሮች ከተመረጡ የስራ መስኮች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል። ከሁለት ዓመት በፊት ግንባታው ተጠናቆ ኢንቨስተሮች ማስተናገድ የጀመረው የመቐለ ኢንዳስትሪ ፓርክ ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ ማደግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩም ተጠቅሷል። የኢንዱስትሪ ፓርኩ 15 ሼዶች ያሉት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ሼዶች በሀገር ውስጥና ውጭ ባለሀብቶች መያዛቸው ተነግሯል። 
በኢንቨስትመንት ፍሰት ዙርያ ሐሳባቸው የሰጡን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህሩ ዶክተር ሙዑዝ ሓዱሽ በበኩላቸው ግልፅ የኢንቨስትመንት መርህ ይዞ የሚሰራ መንግስት ለኢንቨስተሮች የተሻለ መተማመን ይፈጥራል ይላሉ። በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት በተጨማሪ የክልሉ መንግስትም ለኢንቨስተሮች አመቺ ሁኔታ መፍጠሩ፣ ቢሮክራሲው ማስተካከሉ፣ ሰላምና መረጋጋት ማረጋገጡ በመጥቀስ አካባቢው ተመራጭ እንዲሆን ማድረጉ ይገልፃሉ። 
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2.5 ቢልዮን ዶላር ገደማ ካፒታል ያስመዘገቡ የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መውሰዳቸው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን መረጃ ያመለክታል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር አቶ አንተነህ አለሙ በሀገሪቱ ካለው የፀጥታ ሁኔታ አንፃር አሁን ያለው የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት የሚበረታታ ነው ይላሉ።  ከዚህ በተጨማሪ በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታየ ያለው የኤሌክትሪክ ሐይል መቆራረጥ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የፖለቲካ ቀውስ ኣንዲሁም ሌሎች የኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች በትግራይ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያለው ኢንቨስትመንት እንዳይጎዳው ምሁራን ስጋታቸው ይገልፃሉ።

Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie


ሚሊዮን ኃይለሥላሴ


አዜብ ታደሰ