1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ከሞላ ጎደል መረጋጋት እየታየ ነዉ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 18 2011

የአማራና የክልል ከተሞች ከቅዳሜዉ የክልሉ ባለስልጣናት ግድያ ወዲህ ዛሬ የተሻለ መረጋጋት ታይቷል። በደሴ እና  በባሕር ዳር ከተሞች ግን አሁንም ውጥረት መኖሩን የአካባቢዉ ነዋሪዎች እየገለፁ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3L4de
Äthiopien Felege Hiwot-Krankenhaus Katarakt-OP
ምስል DW/A. Mekonnen

የባሕር ዳር እና አካባቢው ውሎ

 

በተለይ ግድያው በተፈፀመባት በባሕርዳር ከተማ የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎች በየቦታዉ በርከት ብለዉ እንደሚታዩ ተገልጿል። በጀነራል አሳምነዉ ፅጌ የትውልድ ከተማ ላሊበላም ተመሳሳይ ውጥረት ሰፍኖ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ስዓት ግን መረጋጋት መታየቱን የአካባቢዉ ባለስልጣናት መግለፃቸው ተሰምቷል።  ዝርዝር ዘገባውን የባሕር ዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን በስልክ አስተላልፎልናል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ