1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ከተፈናቀሉ ወደ ቀያቸው የተመለሱት 40 ሺሕ ገደማ ብቻ ናቸው ተባለ 

ቅዳሜ፣ ሰኔ 8 2011

አማራ አቀፍ ልማት ማህበር የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በለንደን የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር አካሔደ። እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ከተካሔዱ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብሮች ቃል ከተገባው  650 ሚሊዮን ብር ወደ 350 ሚሊዮን የሚሆነው መሰብሰቡን የልማት ማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3KWaG
Großbritannien London | Melaku Fenta Amhara Development Association CEO
ምስል DW/H. Demissie

በክልሉ 107 ሺሕ ገደማ ተፈናቃዮች ይገኛሉ

አማራ አቀፍ ልማት ማህበር የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በለንደን የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር አካሔደ። እስካሁን የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተካሔዱ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብሮች ቃል ከተገባው  650 ሚሊዮን ብር ወደ 350 ሚሊዮን የሚሆነው መሰብሰቡን የልማት ማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። አቶ መላኩ እንዳሉት በክልሉ ከተፈናቀሉ ዜጎች እስካሁን ወደ ቀያቸው የተመለሱት ወደ 40 ሺሕ ገደማ ብቻ ናቸው። በክልሉ ከ107 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። 
ሐና ደምሴ
እሸቴ በቀለ