1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዉሮፕላን የመረጃ ቋት ላይ የሲቪል አቪየሽን ባለሞያ አስተያየት  

ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2011

የኢትዮጵያዉያም ሆነ የኤንዶኔዥያዉ አዉሮፕላን አደጋ ተመሳሳይነት ከተነገረ በኋላ በአውሮፕላን ፋብሪካዉ ቦይንግ ላይ ጫናውን እያጠናከረ መጥቶአል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ የ189 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ንብረትነቱ የኢንዶኔዢያ ከሆነው የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3FMR9
Äthiopien Addis Abeba - Ethiopian Airlines
ምስል G. T. Hailegiorgis

ከአንድ ሳምንት በፊት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን፤ ከወራት በፊት ኢንዶኔዢያ ውስጥ ከደረሰው አደጋ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው አመላካች መረጃ መገኘቱተከትሎ የዓለም ሃገራት አዉሮፕላኑ በየሃገራቸዉ ሰማይ ላይ እንዳይበር አግደዋል። የኢትዮጵያዉያም ሆነ የኤንዶኔዥያዉ አዉሮፕላን አደጋ ተመሳሳይነት ከተነገረ በኋላ በአውሮፕላን ፋብሪካዉ ቦይንግ ላይ ጫናውን እያጠናከረ መጥቶአል።  የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ክስተቱ ባለፈው ጥቅምት ወር ጃካርታ ላይ የ189 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ንብረትነቱ የኢንዶኔዢያ ከሆነው የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ገልጿል። ኢትዮጵያ የተከሰከሰዉ አዉሮፕላን የመረጃ ማጠራቀምያ ሳጥን ምርመራ አንድ ወር ይፈጃል ተብሎአል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግጊዘብሔር በኢትዮጵያ ሲቪል አብየሽን ከ 30 ዓመት በላይ ያገለገሉ ባለሞያን በአዉሮፕላን የመረጃ ሳጥን ጉዳይ ላይ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርጎ  ልኮልናል።

 
ዮሐንስ ገብረግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ