1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባና ኦሮሚያ በኮሌራ የተያዘ ሰዉ ቁጥር መጨመረ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 11 2011

በኢትዮጵያ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እስከ ባለፈው ሳምንት ከተመዘገበው የ16 ሰዎች ሞት በላይ የሞት ጉዳት ባይከሰትም ስርጭቱ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል መጨመሩን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።

https://p.dw.com/p/3KeEd
Bakterien Erreger der Cholera
ምስል picture-alliance/Dr.Gary Gaugler/OKAPIA

የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እስከ ባለፈው ሳምንት ከተመዘገበው የ16 ሰዎች ሞት በላይ የሞት ጉዳት ባይከሰትም ስርጭቱ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል መጨመሩን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። በአዲስ አበባ በ9 ክፍለ ከተሞች፣ በኦሮሚያ፣ ትግራይና አማራ ክልሎች ተከስቷል የተባለው ኮሌራ በአንጻራዊነት በትግራይና አማራ ክልልሎች ካለፉት 10 ቀናት ወዲህ የተያዘ ሰው ሪፖርት አለመቅረቢና ስርጭቱ እየቀነሰ ነው ብሏል ተቋሙ። የኢቦላ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ ባይገባም፣ ከአየር መንገድ ጋር ተያይዞ ችግሩ ሊከሰት የሚችልበት እድል በመኖሩ ከፍተኛ የጥንቃቄ ስራ እየተከናውነ መሆኑም በመግለጫው ተዳስሷል።

Äthiopien PK Beyene Moges in Addis Abeba
ዶ/ር በየነ ሞገስ፦ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ኃላፊምስል DW/S. Muchie

በሌላ በኩል በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የወባ፣ የኩፍኝ ወረርሽኝ በሰዎች ላይ፤ በቀላሉ ወደ ሰው የሚተላለፈው ጊኒ ዎርም ደግሞ በእንስሳት ላይ ተከስቷል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያልተለመደ፣ ታይቶም የማይታወቅና መድሃኒትም ሆነ ክትባት የሌለው በትንኝ ንክሻ የሚተላለፍ «ችኩን ጉንያ» የተባለ ተላላፊ ወረርሽኝ በሶማሌ ክልል መከሰቱ ተነግሯል።  


ሰለሞን  ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ