1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ክልል የሚታየዉ ያለመረጋጋት የቱሪዝም ፍሰትን እያዳከመ ነዉ 

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2011

በደቡብ ክልል የሚታዩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ለቱሪዝም ዘርፍ መቀዛቀዝ ምክንያት እየሆኑ መምጣታቸውን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተናገሩ፡፡ በክልሉ በሆቴልና በአስጎብኚነት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች እንደሚሉት ከሆነ የውጪና የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሽቆለቆለ ይገኛል፡፡

https://p.dw.com/p/3ByXa
Tourismus in Äthiopien
ምስል SNNPR/Tourism and Culture Office

የውጪና የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር አሽቆልቁሏል

በደቡብ ክልል የሚታዩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ለቱሪዝም ዘርፍ መቀዛቀዝ ምክንያት እየሆኑ መምጣታቸውን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተናገሩ፡፡ በክልሉ በሆቴልና በአስጎብኚነት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች እንደሚሉት ከሆነ በክልሉ በድንገት የሚከሰቱ ግርግሮችና ሁከቶች ወደ ክልሉ የሚገቡ የውጪና የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥርን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሽቆለቁል እያደረገው ይገኛል፡፡  የደቡብ ክልል ባህል፤ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በበኩሉ ባለፉት ስድስት ወራት አምስት ሚሊዮን የውጪና የአገር ውስጥ ጊብኚዎችን ለማስተናገድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ወደ ክልሉ የገቡት ጎብኚዎች ቁጥር ግን ከአንድ ሚሊዮን መብለጥ አንዳልቻሉ አስታውቋል፡፡ 


ሸዋንግዛው ወጋየሁ


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ