1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን የመጀመሪያው ጥቁር የባቡር ሾፌር

Tamirat Geletaዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

https://p.dw.com/p/4d6Mp

ጊዜው ክረምት ነው፡፡ የጎርጎርሳውያኑ 1896፡፡ ኩዋን ማርቲን ዲቦቤ የተባለ ካሜሩናዊ በርሊን ውስጥ በሚገኘው ትሬፕ ታወር ፓርክ ውስጥ ቆሟል፡፡ ዲቦቤ የአስከፊው የጀርመን ቅን አገዛዝ ማሳያ በሆነው የሰው ልጅ ለእይታ በሚቀርብበት አውደ ርዕይ ላይ ለመታየት ከቀረቡ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ብርቱ ሰው  የኋላ ኋላ ግን ጀርመን  ከቅኝ ግዛቶቿ ጋር ያላትን ኢ-ፍትሃዊ ግንኙነትን በመፋለም የሰብዓዊ መብት ተሟጋችነትን ስለመምራቱ የሚያውቁት በእርግጥ ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ኩዋን ማርቲን ዲቦቤ ምናልባትም ጀርመን ውስጥ በደንብ የሚታወቀው በሀገሪቱ የመጀመሪያው ጥቁር የባቡር ሾፌር በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በ1900ዎቹ ምን ያህል በቴክኖሎጂ ተራምደን እንደነበር ሳያሳይ አይቀርም፡፡ ምናልባትም ከዛሬ ሁኔታም በተሻለ ሁኔታ ፡፡  ያ በእግጥ ለእርሱ መንገድ ሆኖታል፡፡ በህይወቱ የገጠመው የተሻለ መንገድ፡፡#የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ #Shadows of German colony

አዘጋጅ ካይ ኔቤ

ተርጓሚ እና ተራኪ ታምራት ዲንሳ