1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች

ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2011

በመላው ዓለም በየዓመቱ 41 ሚሊየን የሚሆን ሕዝብ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ሕይወቱን እንደሚያጣ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል። ይህም በመቶኛ ሲሰላ  71 በመቶ ይደርሳል።

https://p.dw.com/p/37Wxh
Junger Mann mit Herzschmerzen
ምስል picture-alliance/Bildagentur-online/Begsteiger

ኢትዮጵያ ውስጥም ጉዳታቸው እየታየ ነው

ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ከሚሞቱት መካከልም 15 ሚሊየኑ እድሜያቸው በ30 እና 69 ዓመት መካከል የሚገኝ ነው። ከተጠቀሰው ላይ 85 በመቶ የሚሆነው ሞት የሚደርሰውም ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባለባቸው ሃገራት እንደሆነም ከአራት ወራት በፊት ድርጅቱ ይፋ ያደረገው መረጃ ይዘረዝራል። ከመቀሌ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ የላከው ዘገባ ኢትዮጵያ ውስጥም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያደርሱት ጉዳት እየጨመረ መሄዱን ያመለክታል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ