1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዋሚዎችን ያላሳተፈው የኢኳቶርያል ጊኒ ብሔራዊ ውይይት

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 14 2010

በኢኳቶርያል ጊኒ የአምስት ቀናት ብሔራዊ ውይይት ተካሄደ። ውይይቱን የጠሩት ሀገሪቱን ከጎርጎሪዮሳዊው 1979 ዓም ወዲህ በመምራት ላይ የሚገኙት ፕሬዚደንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጌማ ናቸው።

https://p.dw.com/p/31qEZ
Teodoro Obiang, Präsident Äquatorialguinea
ምስል picture-alliance/Zumapress/C. Mahjoub

«ለይስሙላ የተደረገው ብሔራዊ ውይይት በፖለቲካ ስርዓቱ ላይ ተሀድሶ አላስገኘም።»

ባለፈው ሀምሌ 11፣ 2018 ዓም የተጠራው ሁሉን የህብረተሰቡን ክፍል እንዲያሳትፍ የተፈለገው ብሄራዊው ውይይት ዓላማ የሀገሪቱን ሰላም ማስጠበቅ እና ልማቷንም ወደፊት ማራመድ ነው ።  ፕሬዚደንቱ ይህን ዓይነት ውይይት ሲጠሩ የሰሞኑ ስደተኛ ጊዜ ሲሆን፣ በዚሁ ውይይት ላይ የተቃዋሚ ቡድኖች ተወካዮች፣ የሲብሉ ማህበረሰብ እና የሀይማኖች ቡድኖች ተወካዮች  ተጋብዘዋል።   በስደት በዩኤስ አሜሪካ በሚኖሩት የተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቱቱ አሊካንቴ  እይታ፣ የስድስት ቀኑ የይስሙላሰሞኑ ውይይትም እንዳለፉት ውይይቶች ሁሉ ውጤት አላስገኝም።
«  ካለፉት ብሔራዊ ውይይቶች በኋላ ምን የተሰራ ነገር አለ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል። በውይይቶቹ የተሳተፉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንደሚሉት፣ የተካሄደው ውይይት ሳይሆን ፕሬዚደንቱ ብቻ የተናገሩበት ስብሰባ ነበር። »
ፕሬዚደንት ኦቢያንግ ውይይቱ ከመጀመሩ በፊት የውይይቱ ተሳታፊዎቹ፣ በተለይ ፣ በስደት የሚኖሩት ተቃዋሚዎች የመናገር ነፃነታቸው እንደሚጠበቅላቸው፣ በግል ከለላ እንደሚደረግላቸው እና በነፃ መዘዋወር እንደሚችሉ  ቃል ገብተዋል። ይህ የፕሬዚደንት ኦቢያንግ ቃል መጠበቁን የሚጠራጠሩት ተጋባዦች የስድስት ቀኑ ብሔራዊ ውይይት በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ተሀድሶ ለውጦች የሚደረግበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት ይላሉ። ለውጦቹ  ነፃ ምርጫ ማድረግ፣ ነፃ የመገናኛ ብዙኃን እና የመናገር ነፃነትን ማጠቃለል ይኖርባቸዋል። ይሁን እንጂ፣ ቀደም ሲል የተዘረዘሩት ሀሳቦች በፕሬዚደንት ኦቢያንግ የውይይት አጀንዳ ውስጥ ቅድሚያ አላገኙም፣ ኦቢያንግ ውይይቱን የተመለከቱት  ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላቸው እና ይህን እውን ማድረግ ስለሚችሉበት እቅዳቸው ለተሳታፊዎች ማብራራያ የሚሰጡበት አጋጣሚ ነው ። ኦቢያንግ ለተሳታፊዎች ደህንነት የገቡትንም ቃል ሆነ በፖለቲካ ስርዓቱ ላይ ተሀድሶ ማድረግ የሚለውን ሀሳባቸውን ግን ቱቱ አሊካንቴን የመሳሰሉ የተቃዋሚ ፖለቲከኖች እንደማያምኑት ነው ለዶይቸ ቬለ የተናገሩት።
« ለደህንነቴ ስለምሰጋ ወደ ኢኳቶርያል ጊኒ አልሄድም። በዚያ ባልኖርም ያላጠፋሁትን ጥፋት ሰርተሀል ብለው ሊያስሩኝ ይችላሉ። በሀገሪቱ ያለው አሰራር ይህ ነው። እኛን ሊከላከል የሚችል ሕግ የለም። በኢኳቶርያል ጊኒ ውስጥ ፖለቲካዊ ውይይት ሊካሄድ የሚያስችል የሕግ የበላይነት የለም። »
ኦቢያንግ በመንግሥቱ እና በተቃዋሚ ቡድኖች መሪዎች መካከል እንዲደረግ ለጠሩት ብሔራዊው ውይይት መንገዱን ለማመቻቸት በማሰብ ከሁለት ሳምንት በፊት የምሕረት አዋጅ በማውጣት የፖለቲካ እስረኞችን በጠቅላላ እንደሚፈቱ ተናግረው ነበር። እንደሚታወሰው፣ ባለፈው ታህሳስ ወር በፕሬዚደንት ኦቢያንግ ላይ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ ከተካሄደ በኋላ በተከተሉት ጥቂት ወራት መንግሥት በተቃዋሚው ቡድኖች ላይ ባሳረፈው ብርቱ ክትትል ብዙ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ታስረዋል።  በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሁሌ የሚያቀርቡትን ይህን ዋነኛ ቅድመ ግዴታ መንግሥት ለማሟላት ዝግጁ መሆኑ በአዎንታዊነት ነው የተመለከቱት።  እርግጥ፣ አንዳንድ  ተቃዋሚ ፖለቲከኖች ተፈተዋል።  ይሁንና፣ የተቃዋሚ ቡድን ፖለቲከኞች አሁንም በሀገሪቱ ወህኒ ቤቶች በእስር ላይ ስለሚገኙ አምስት በስደት የሚገኙ ዋነኛ የሚባሉ የተቃዋሚ ቡድኖች ተወካዮች ከዚሁ ብሔራዊ ውይይት ርቀዋል። ሲቲዘን ፎር ኢኖቬሽን፣ በምህጻሩ ሲ አይ የተባለው ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ባለፈው የካቲት ወር ታግዶ፣ ብዙ አባላቱ ታስረው ነበር። አንዳንዶች በምሕረቱ አዋጅ ቢፈቱም ሌሎች እንደታሰሩ ይገኛል።   ስብሰባው ከመዲናይቱ ማላቦ ውጭ በሌላ ሀገር ቢካሄድ ኖሮ ሊሳተፉ ይችሉ እንደነበር ገልጸዋል። 
1,2 ሚልዮን ሕዝብ የሚኖርባት ኢኳቶርያል ጊኒ ከምትገኝበት የመገለል ሁኔታ ለመላቀቅ ባደረገችው ጥረት በ2014 ዓም የፖርቱጋል ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት ማህበረሰብ፣ በምህጻሩ፣ የሲፒኤልፒ አባል ሆናለች፤ በአፍሪቃ ካሉት ትልቆቹ የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው የኢኳቶርያል ጊኒ ርዕሰ ብሔር ኦቢያንግ ሀገራቸው የዚሁ ድርጅት አባል ትሆን ዘንድ የሞቱን ቅጣት ለመሻር እና የሰብዓዊ መብትን ለማክበር  ቃል ገብተው ነበር። የሞቱ ቅጣት ከመሻሩ ባለፈ፣ ሌላ የተሰራ ነገር እንደሌለ የሀገራትን የሙስና ደረጃ የሚመረምረው ዓለም አቀፍ ድርጅት ፣ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባልደረባ ዦዋዎ ፓውሎ ባታላ ይናገራሉ።
« በሀገሪቱ በስልጣን አላግባብ የመጠቀም አሰራር ይታያል። ስርዓተ ዴሞክራሲን ለማስፈን ኢኳቶርያል ጊኒ በተደጋጋሚ የገባችው ቃል ወሸት ሆኖ ነው የተገኘው። በመሆኑም፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሉዞ አባል ሀገራት ርምጃ መውሰድ ነበረባቸው። አባልነቷ ስርዓተ ዴሞክራሲ ለሚሰፍንበትን ድርጊት  ያፋጥናል የሚል አመለካከት የያዘው ሉዞ በተለይ ይህን የመከታተል ኃላፊነት አለበት። ይሁንና፣ እስካሁን በዚሁ ረገድ ምንም አላደረገም።»

Karte Äquatorialguinea ENG
Äquatorialguinea 2016 Präsidentschaftswahl
ምስል Getty Images/AFP/STR

አርያም ተክሌ/አንቶንዮ ካሽካሽ

ተስፋለም ወልደየስ