1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቶጎ ፤ «የአብነት ቅኝ ግዛት»

Tamirat Geletaሰኞ፣ መጋቢት 9 2016

በጎርጎርሳውያኑ ሃምሌ 1884 የጀርመን ንጉሰነገስት ባንዲራ አፍሪቃ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰቀለው ከታንዛንያ እና ናሚቢያ ቀድሞ ቶጎ ውስጥ ነበር ። ለ30 ዓመታት በዘለቀው የቅኝ ግዛት ዘመን ከሌሎቹ ግዛቶች አንጻር ሰላማዊ የመሰለ አገዛዝ ስለሆነላቸው ጀርመኖቹ በሞግዚት የምትተዳደረው ትንሿን ቶጎ «የአብነት ቅኝ ግዛት» በማለት ሰይመዋል።

https://p.dw.com/p/4cnKT

 የጀርመን አስከፊ ቅኝ አገዛዝ አስከፊ ታሪክ ቅሪት 

በጎርጎርሳውያኑ ሃምሌ 1884  የጀርመን ንጉሰነገስት ባንዲራ አፍሪቃ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰቀለው ከታንዛንያ እና ናሚቢያ ቀድሞ ቶጎ ውስጥ ነበር ። ለ30 ዓመታት በዘለቀው የቅኝ ግዛት ዘመን ከሌሎቹ ግዛቶች  አንጻር ሰላማዊ የመሰለ አገዛዝ  ስለሆነላቸው ጀርመኖቹ በሞግዚት የምትተዳደረው ትንሿን ቶጎ እንደ «የአብነት ቅኝ ግዛት» ወስደዋል። ነገር ግን እነዚሁ የቅኝ ግዛት  አስተዳዳሪዎቹ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያስከብሩበትን  መንገድ ብቻ ይከተሉ ነበር።

 አውሮጳውያን በምዕራብ አፍሪቃ የባህር ዳርቻዎች ለክፍለ ዘመናት የዘለቀ የንግድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አካባቢው በአውሮፓ ካርታ ሠሪዎች ዘንድ የባሪያ ንግድ ጠረፍ ተብሎ ይታወቅ የነበረ ሲሆን  የባርነት ንግዱም እስከ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የዘለቀ ነበር። በባሪያ ንግድ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የአካባቢው ቡድኖች በንግዱ ትርፋማ ነበሩ ። የጀርመን ቅን ገዢ ጦር አዛዥ  ጉስታቭ ናችቲጋል በ1884 ከኤው ንጉስ ምላፓ 3ኛ ጋር የሞግዚትነት አስተዳደር  ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት የቶጎ ልሂቃን ከተለያዩ የአውሮጳ ቅን ገዢዎች ጋር ግንኙነት ያደርጉ ስለነበር ስጋት አልነበሩም ። ከዚህ ይልቅ ግን በውስጥ የሚያደርጉት የእርስ በእርስ ግጭት እና ጦርነት ጎልቶ ይታይ ነበር ።#የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ #Shadows of German colonialism

አዘጋጅ ካይ ኔቤ

ተርጓሚ እና ተራኪ ታምራት ዲንሳ