1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አለምዬ ጌታቸው (ዋሸሁእንዴ?)

እሑድ፣ ሐምሌ 8 2010

እናት አባቱ ያወጡለት መጠሪያ ስሙ ዓለማየሁ ጌታቸው ነው። በቤተሰብም ሆነ በሰፈር ግን ዓለምዬ ተብሎ እየተጠራ አድጓል። የለመደው በመሆኑ ዓለምዬ ቢባል ይመርጣል። ለሙዚቃ ያለው ፍላጎት ተወልዶ ያደገበት አዲስ አበባ ኳስ ሜዳ በመባል የሚታወቀው ሰፈር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።

https://p.dw.com/p/30vCb
Alemye Getachew - Äthiopischer Sänger
ምስል DW/S. Legesse

24.06.2018 ዋሸሁ እንዴ?

 ከእዚያ ዛሬ እውቅና እና ዝና ያተረፉ አንጎራጓሪዎች ወጥተዋል። አርቲስት ዓለምዬ እንደሚለው እነሱ የሕጻንነት ቀልቡን ወስደው ከሙዚቃ አቆራኝተውታል። እናም አንተ ዘፋኝ ባትሆን ምን ትሆን ነበር ስለው ሳቅ ቀደመው፤ እንጃ ሌላ ዘፋን እሆን ነበር ሲልም አከለ። አዎ ዋሸሁ እንዴ? ብዬ እኔም ልጠይቀው መሰል፤ ዝናን ባተረፈለት ዜማው ቅላጼ። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ