1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምነስቲ ወጣቶች በብዛት የታሰሩበትን ሁኔታ አወገዘ 

ማክሰኞ፣ መስከረም 15 2011

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአዲስ አበባ ፖሊስ በሰሞኑ ሁከት እና ግርግር ሰበብ በርካታ ወጣቶችን ማያሰረበትን እና የታሰሩበት አያያዛቸዉ ሰብዓዊ መብታቸዉን ያላከበረ ነዉ ሲል ርምጃውን በማውገዝ መግለጫ አወጣ።

https://p.dw.com/p/35TyF
Logo Amnesty International

የወጣቶች መታሰርና አምነስቲ

መንግሥት ስርዓት ለማስከበር ርምጃ መውሰዱ ትክክል ቢሆንም ሕግን ባከበረ መንገድ መሆን እንዳለበት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብአዊ መብት አጥኚ አቶ ፍሰሐ ተክሌ ዛሬ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።  ወደ ጦር ማሰልጠኛ ቦታዉ ወደ ጦላይ የተወሰዱት ወጣቶች የሰብዓዊ መብታቸዉ እና የመንቀሳቀስ መብታቸዉ መጣሱን፣ እንዲሁም፣ ጫትና ሺሻ በሃገሪቱ ደንብ ሕገ ወጥ ነዉ በሚል የወጣ ምንም ዓይነት ሕግ አለመጽደቁንም አቶ ፍስሐ አክለው አስታውቀዋል።

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ