1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምንስቲ፤ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን  ማሻሻያ ያስፈልገዋል

ሰኞ፣ ሰኔ 10 2011

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ያወጣቸው የምርመራ ሪፖርቶች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ማዕቀፎችን እና ደረጃዎችን የተከተሉ አልነበሩም ሲል ገለፀ። በፍትህ ላይ የሚፈጸሙ መዛባቶችን ለማስተካከል በመንግስታዊው የሰብዓዊ ተቋም ላይ ማሻሻያ ይደረግ ሲል አሳስቧል። 

https://p.dw.com/p/3Karv
Logo von Amnesty International

«ኮሚሽኑ ለምርመራ የተከተላቸው ዘዴዎችና የምርምራ ግኝቶቹ “ጉልህ ክፍተት አለዉ» አምንስቲ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ያወጣቸው የምርመራ ሪፖርቶች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ማዕቀፎችን እና ደረጃዎችን የተከተሉ አልነበሩም ሲል ገለፀ። በፍትህ ላይ የሚፈጸሙ መዛባቶችን ለማስተካከል በመንግስታዊው የሰብዓዊ ተቋም ላይ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት አምንስቲ አሳስቧል። አምንስቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በጎርጎሮሳዊው 2016 እና 2017 ዓ. ም. የታተሙ ሰባት የኮሚሽኑን የምርመራ ሪፖርቶችን መፈተሹን ገልጿል። ኮሚሽኑ ተፈጸሙ በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምርመራዎችን ሲያደርግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁ የሰብዓዊ መብት ማዕቀፎች እና ደረጃዎች ውጭ ይንቀሳቀስ እንደነበር በፍተሻው ደርሼበታለሁ ብሏል። ኮሚሽኑ ለምርመራ በተከተላቸው ዘዴዎች እና በምርምራ ግኝቶቹ ላይ “ጉልህ ክፍተት” ማግኘቱን አምንስቲ በመግለጫው ጠቁሟል። ዶቼ ቬለ «DW» ያነጋገራቸዉ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተመራማሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ እንደተናገሩት ፤ ከተፈተሹት ሪፖርቶች መካከል  በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በነበሩ ተቃውሞዎች ላይ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ፤ እንዲሁም በጎርጎረሳዉያኑ 2016 ኢሬቻ ክብረ በዓል ክስተትን ይመለከታል። ሬፖርቶቹ ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረቡ እና ምክር ቤቱ አጽድቆ ያሳለፋቸዉ ነበሩ ብለዋል። አቶ ፍስሃ ተክሌን ስለድርጅቱ መግለጫ አነጋግረናቸዋል።      


አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ