1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አርቲስት ሱዚ ተጫኔ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 10 2010

የሥዕል ጥበብን ከዕደ ጥበብ ጋር አዋህዳ የምትሰራው አርቲስት ሱዚ ተጫኔ የተወለደችው አዲስ አበባ ይሁን እንጂ አስተዳደግዋ ግን  አዲስ አባባን አቋርጦ ድሬዳዋን ጨምሮ ናይጀሪያን ተሻግሮ ፈረንሳይ ድረስ ይዘልቃል።

https://p.dw.com/p/33HZt
Suzi Techane
ምስል DW/H. Tiruneh

አርቲስት ሱዚ ተጫኔ

ያደገችው በቅይጥ ባህል ነው። ይሁን እንጂ በጥበብ ሥራዎችዋ ጎልተው የሚወጡት ኢትዮጵያዊ የግዕዝ ፊደላት፣ ኢትዮጵያዊ ቀለማት እና ኢትዮጵያዊ መልኮች ናቸው። የሥዕል ጥበብን ከዕደ ጥበብ ጋር አዋህዳ የምትሰራው አርቲስት ሱዚ ተጫኔ የተወለደችው አዲስ አበባ ይሁን እንጂ አስተዳደግዋ ግን  አዲስ አባባን አቋርጦ ድሬዳዋን ጨምሮ ናይጀሪያን ተሻግሮ ፈረንሳይ ድረስ ይዘልቃል። የዛሬው የባህል መድረክ እንግዳችን ባለፉት 27 ዓመታት ኑሮዋን በሀገረ ፈረንሳይ በልዮ ከተማ ያደረገችውን ኢትዮጵያዊት የጥበብ ባለሞያ ሱዚ ተጫኔን ያስተዋውቀናል። 


ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ