1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭት እና የደቦ ጥቃት በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ነሐሴ 13 2010

ወጣቶች በስሜታዊነት ይፈጽሟቸዋል በሚባሉ የደቦ ጥቃቶች የሰው ህይወት እየጠፋ፣ ንብረት እየወደመ፣ እንቅስቃሴዎችም እየተገቱ እና እየተስተጓጎሉ መሆናቸው ነው የሚነገረው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሳውን ግጭት፣ ሁከት እና ልዩ ልዩ ጥፋቶችን ለማስቆም አለያም ለመከላከል የፀጥታ ኅይሎች ፈጥነው አልደረሱም መባሉም ማጠያየቁ ቀጥሏል።

https://p.dw.com/p/33NB7
Äthiopien Gedeb Binnenflüchtlinge aus West-Guji
ምስል picture-alliance/dpa/World Vision/Fitalew Bahiru

ውይይት፦ ግጭት እና የደቦ ጥቃት በኢትዮጵያ

ዶክተር ዐብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር  ከሆኑበት ከዛሬ አራት ወራት አንስቶ ኢትዮጵያ በለውጥ ጎዳና ላይ ናት። አንድነትን የሚያቀነቅነው ፈጣኑ ለውጥ ህብረተሰቡን በማነቃቃት እና ተስፋም በማሳደር ቀጥሏል። ይሁን እና ከለውጡ ጎን ለጎን በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ድንገተኛ ግጭቶች ግድያ ዝርፊያ እና ሰዎችን ማፈናቀል ከመቆም ይልቅ እዚህም እዚያም መቀጠሉ ማስጋቱ አልቀረም። ከነዚሁ ክስተቶች ጎን ለጎን በተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች በደቦ እና በግብታዊነት ይፈጽማሉ የሚባለው ጥቃት ሌላው አሳሳቢ እና አጠያያቂ ጉዳይ ሆኗል።

ወጣቶች በየአካባቢው «ያልተረጋገጡ» መረጃዎችን መነሻ አድርገው በስሜታዊነት ይፈጽሟቸዋል በሚባሉ የደቦ ጥቃቶች የሰው ህይወት እየጠፋ፣ ንብረት እየወደመ፣ እንቅስቃሴዎችም እየተገቱ እና እየተስተጓጎሉ መሆናቸው ነው የሚነገረው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሳውን ግጭት ፣ ሁከት እና ልዩ ልዩ ጥፋቶችን ለማስቆም አለያም ለመከላከል የፀጥታ ኅይሎች ፈጥነው አልደረሱም መባሉም ማጠያየቁ ቀጥሏል። በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደርሰው ግጭት እና የወጣቶች የደቦ ጥቃት የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው።  

በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ አራት እንግዶችን ጋብዘናል። እነርሱም ዶክተር አወል ቃሲም አሎ በኪል-ብሪታንያ ዩኒቨርስቲ የሕግ ረዳት ፕሮፌሰር፣ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር፣ አቶ ሀሌሉያ ሉሌ የፖለቲካ እና የደህንነት ጉዳዮች ተንታኝ እንዲሁም ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ገቢሳ በአሜሪካን ኬተሪንግ ዩኒቨርስቲ የባህል እና ቴክኖሎጂ መምህር እንዲሁም የኦሮሞ ሚድያ ኔት ወርክ አማካሪ ናቸው። ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ በመጫን ሙሉውን ውይይት ማዳመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ