1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአበርገሌው ድርቅ እና ረሃብ

ረቡዕ፣ የካቲት 6 2016

በማዕከላዊ ትግራይ ዞን በምትገኘው አበርገሌ ወረዳ የተከሰተው ድርቅ እና ረሃብ አሳሳቢ መሆኑን የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ከስፍራው ተመልክቷል። በድርቁ ምክንያት እየቀረበ ያለው ዕርዳታም ከተከሰተው ድርቅ ጋር የማይመጣጠን እንደሆነ ከአካባቢው አስተዳደር ተረድቷል። ድርቁ ከ80 በላይ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል።

https://p.dw.com/p/4cOdJ
Äthiopien Abergele Tigray | Unterernährung
ምስል Million Haileselasie/DW

በአበርገሌው ድርቅ እና ረሃብ በርካቶች ከአካባቢው ተሰደዋል

በማዕከላዊ ትግራይ ዞን በምትገኘው አበርገሌ ወረዳ የተከሰተው ድርቅ እና ረሃብ አሳሳቢ መሆኑን የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ከስፍራው ተመልክቷል። በድርቁ ምክንያት እየቀረበ ያለው ዕርዳታም ከተከሰተው ድርቅ ጋር የማይመጣጠን እንደሆነ ከአካባቢው አስተዳደር ተረድቷል። ከችግር ያልተላቀቁት የአበርገሌ ወረዳ አካባቢዎችአካባቢው ከሁለት ዓመታቱ ደም አፋሳሽ ጦርነት ጠባሳ ገና ባልሻረበት ሁኔታ የተከሰተው ድርቅ ከ80 በላይ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል።

አበርገሌ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ያለች ህጻን
ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ እንስሳትም የድርቁ ሰለባ ሆነዋል። በአካባቢው እስካሁን ዝናብ አለመዝነቡ ደግሞ በአካባቢው የተከሰተውን ድርቅ እና ረሃብ እንዳያባብሰው አስግቷል። እንደዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ በአካባቢው ዝናብ የመዝነብ አዝማሚያ ተስፋም አይታይም ።ምስል Million Haileselasie/DW

ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ እንስሳትም የድርቁ ሰለባ ሆነዋል። በአካባቢው እስካሁን ዝናብ አለመዝነቡ ደግሞ በአካባቢው የተከሰተውን ድርቅ እና ረሃብ እንዳያባብሰው አስግቷል። እንደዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ በአካባቢው ዝናብ የመዝነብ አዝማሚያ ተስፋም አይታይም ። ድርቁን ተከትሎ በተፈጠረው ረሃብ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለመሰደድ ተገደዋል። 

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ